You are currently viewing አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከሳምንታት በፊት አንድ ሰው አቁስሎ ከ380 በላይ የቀንድ ከብቶችን በዘረፈበት በጉለንቴ ቀበሌ ለሁለተኛ ዙር ተኩስ ከፍቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት 3 ቀን…

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከሳምንታት በፊት አንድ ሰው አቁስሎ ከ380 በላይ የቀንድ ከብቶችን በዘረፈበት በጉለንቴ ቀበሌ ለሁለተኛ ዙር ተኩስ ከፍቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 3 ቀን…

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከሳምንታት በፊት አንድ ሰው አቁስሎ ከ380 በላይ የቀንድ ከብቶችን በዘረፈበት በጉለንቴ ቀበሌ ለሁለተኛ ዙር ተኩስ ከፍቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 3 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከሆሮ ጉድሩ ዞን አቢ ደንጎሮ ወረዳ ለአሚማ የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ዛሬ ጥቅምት 3 ቀን 2014 ከቀኑ 10 ሰዓት ተኩል ጀምሮ አሸባሪው ኦነግ ሸኔና ተባባሪዎቹ በጉለንቴ አማራዎች ላይ ተኩስ ከፍተዋል። ተኩሱ ይህበዜና እስከተጠናቀረበት 12 ሰዓት ድረስ እንደቀጠለ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ከአካባቢው ሚሊሾች ውጭ በአቢ ደንጎሮ ሌላ የመንግስት የጸጥታ አካል አለመኖሩን የገለጹት ነዋሪዎች አስቸኳይ ድጋፍ ጠይቀዋል። መስከረም 12 ቀን 2014 በጉለንቴ ቀበሌ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ግብረ አበሮቹ አንድ አርሶ አደርን በማቁሰል ከ380 በላይ የአማራ ከብቶችን ዘርፈዋል፤ በድጋሜ ተመልሰውም ጥቃት ፈጽመው ተመልሰዋል። መስከረም 28 ቀን 2014 በአቢ ደንጎሮ ኢዶክሳ ቀበሌ 7 አህዮችን አርዶ ጥሎ መገኘቱ ብዙዎችን ያሳፈረና ያስቆጣ መሆኑ ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply