አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከነሃሴ 26/2014 ከቀኑ 12: 30 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ በቡኖ በደሌ ዞን ኤሌሞ ወረዳ ወረቦ ቀበሌ ጥቃት መክፈቱ እና ትጥቅ ለማስፈታት እየተንቀሳቀሰ መሆ…

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከነሃሴ 26/2014 ከቀኑ 12: 30 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ በቡኖ በደሌ ዞን ኤሌሞ ወረዳ ወረቦ ቀበሌ ጥቃት መክፈቱ እና ትጥቅ ለማስፈታት እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ነሃሴ 26/2014 ከቀኑ 12: 30 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ በቡኖ በደሌ ዞን ኤሌሞ ወረዳ ጥቃት ከፍቷል። በኤሌሞ ወረዳ ወረቦ በተባለ የገጠር ከተማ ተኩስ በመክፈት አካባቢውን ተቆጣጥረዋል፤ ንብረት እየዘረፉ ነው፤ አሁን ላይም በአንድ ት/ቤት ግቢ ሰፍረው ይገኛሉ ተብሏል። በወረቦ ከተማ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና የልዩ ኃይል አባላት ብዙም ሳይዋጉ ህዝቡን ጥለው መሸሻቸው ተገልጧል። ወደ አካባቢው የገቡት የኦነግ ሸኔ አባላት ቁጥራቸው ከ120 በላይ ይሁኑ እንጅ ቀደም ብለው የገቡ እንዳሉም የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ምንጮች ተናግረዋል። የቀበሌው ሊቀመንበር ከኦነግ ሸኔ ጋር በመስማማት ከኦሮሞ ተወላጆች 8 የጦር መሳሪያ ያስረከበ ቢሆንም አብዛኛው ነዋሪ አማራ ስለሆነ ትጥቄን አልፈታም በሚል ወደ ጫካ መግባቱን ጠቁመዋል። የሚመለከተው አካል አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ጥሪ አድርገዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply