አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከአማራ ጋር የተጋቡ እና በአበልጅነት የተዛመዱ ናቸው በሚላቸው የጃርቴ ነዋሪዎች ላይ ዝርፊያ እየፈፀመ መሆኑ ተገለፀ። አሻራ ሚዲያ መስከረም 5 ቀን 2014 ዓ.ም…

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከአማራ ጋር የተጋቡ እና በአበልጅነት የተዛመዱ ናቸው በሚላቸው የጃርቴ ነዋሪዎች ላይ ዝርፊያ እየፈፀመ መሆኑ ተገለፀ። አሻራ ሚዲያ መስከረም 5 ቀን 2014 ዓ.ም ባህርዳር_ኢትዮጵያ በሆሮ ጉድሩ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ከአማራ ጋር ይተባበራሉ ፣ የተጋቡ ናቸው እንዲሁም በአበልጅነት ተዛምደዋል የተባሉ ኦሮሞዎችም የጥቃቱ ሰለባ እየሆኑ ሲሆን ክርስቲያንና ሙስሊም የሆኑ አማራዎችን ሳይለይ በአማራነታው እየገደለ ያለው የኦነግ ሸኔ ተስፋፊና ዘር አጥፊ ቡድን ከኦሮሞዎችም ክርስቲያኖችን ለይቶ የሚያጠቃበት ሁኔታ መኖሩ ተጠቁሟል። የእነ በቀለ ገርባን የመከፋፈል አላማ እያስፈፀመ ነው የሚሉት የጃርቴ ነዋሪዎች እንደአብነትም መስከረም 4 ቀን 2014 ሌሊት ላይ ከ40 በላይ የሚሆኑ የኦሮሞና የአማራ ከብቶችን መዝረፉን ገልፀዋል። ዝርፊያ ከተፈፀመባቸው ኦሮሞዎች መካከልም በተለይም ከአማራ ጋር የሚግባቡ ፣ የተጋቡና በአበልጅነት ተዛምደዋል የተባሉ እንደሚገኙበት ተገልጧል። ምንም እንኳ አማራን በጠላትነት ፈርጆ እየፈጀ ቢሆንም ከአማራው ቀጥሎ የሚያጠቃቸውን ወገኖች ለይቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ መታወቅ አለበት ያሉት ነዋሪዎች ሁሉም ተረባርቦ እንዲታገለው አሳስበው ከዛ ውጭ ግን የጨካኙን ቡድን ጥቃት ለመቀበል ወረፋ የመጠበቅ ጉዳይ እንደሚሆን ማሳያዎችን በመጥቀስ ጠቁመዋል። ይህ የሽብር ቡድኑ ሌሊቱን ዝርፊያ ከፈፀመባቸው የጃርቴ ነዋሪዎች መካከል አቶ ታምሩ ወ/አገኝ እና አቶ ተሾመ የተባሉ ነዋሪዎች እንደአብነት ተጠቅሰዋል። አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን! ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 Telegram :-https://t.me/asharamedia24 Yotube:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply