You are currently viewing አሸባሪው ኦነግ ሸኔ የጸጥታ አካላትን የደንብ ልብስ በመልበስ ተመሳስሎ በንጹሃን ላይ ጥቃት እየፈጸመ በመሆኑ ወደ አካባቢው ለስምሪት የሚመጡ የመንግስት አካላትን በተመለከተ ቀድሞ መረጃ ሊኖረ…

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ የጸጥታ አካላትን የደንብ ልብስ በመልበስ ተመሳስሎ በንጹሃን ላይ ጥቃት እየፈጸመ በመሆኑ ወደ አካባቢው ለስምሪት የሚመጡ የመንግስት አካላትን በተመለከተ ቀድሞ መረጃ ሊኖረ…

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ የጸጥታ አካላትን የደንብ ልብስ በመልበስ ተመሳስሎ በንጹሃን ላይ ጥቃት እየፈጸመ በመሆኑ ወደ አካባቢው ለስምሪት የሚመጡ የመንግስት አካላትን በተመለከተ ቀድሞ መረጃ ሊኖረን ይገባል ሲሉ የጃርዴጋ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 16 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አንዳንድ የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን አመራሮች ወደ ጃርዴጋ እና አካባቢው የጸጥታ አካላትን ያለ መረጃ ልውውጥ እየላኩ ለግጭት እየዳረጉን ነው ሲሉ ያወገዙት ነዋሪዎች ጥቅምት 16/2015 የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላትን ድንገት በመላክ ምንም እንኳ ጉዳት ባይደርስም ሸኔ ናቸው በሚል ለግጭት እንዲነሳ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል። መስከረም 12 እና 14/2015 ጨምሮ ከአሁን ቀደም ሶስት አራት ጊዜ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊትን የደንብ ልብስ በመልበስ በጃርዴጋ እና አካባቢው አማራዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) አውስተዋል። ጥቅምት 16/2015 ከቀኑ 5 ሰዓት ገደማ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከመስከረም 12/2015 ጀምሮ ከተያዘችው ከጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ዋና ከተማ ጃርቴ አቅጣጫ የመጡ ኦሮሚያ ልዩ ኃይል የደንብ ልብስ የለበሱ አካላት በጃርዴጋ ሚሊሾች ላይ “እናልፋለን፣ አታልፉም፣ እናንተ እነማን ናችሁ?” በሚል ክርክር በመነሳቱ ተኩስ እንደከፈቱባቸው ተገልጧል። አሚማ ስምሪት የተሰጠውን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አመራር እና የአካባቢው ነዋሪዎችን በቀጥታ የስልክ ውይይት በማስገባት እንዲወያዩ እና እንዲስማሙ ለማድረግ ችሏል። በመጨረሻም አሚማ ሁለቱንም አካላት ለማገናኘት ካደረገው እንቅስቃሴ በፊት ጉዳዩን በሀገር ሽማግሌዎችና በኃይማኖት አባቶች ጣልቃ ገብነት እየተነጋገሩበትም ስለነበር በስምምነት ልዩ ኃይሎች ወደሚፈልጉበት አቅጣጫ እንዲያልፉ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል። እንደ አጠቃላይ ከሆሮ ጉድሩም ሆነ ከምስራቅ ወለጋ ዞን ተነስቶ በተደጋጋሚ የመንግስት የጸጥታ አካላትን ልብስ በመልበስ በሸኔ ጥቃት እየተፈጸመበት ወዳለው ጃርዴጋ እና አካባቢው ለስምሪት ከሚመጣ የጸጥታ አካል ጋር ግጭት እንዳይፈጠር ቀድሞ ከሚመለከተው አካል ጋር የመረጃ ልውውጥ ማድረግ የግዴታ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ እንዲገባ ከነዋሪዎች ጥሪ ቀርቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply