አሸባሪው የህወሃት ቡድን በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ በሃሙሲት ከተማ በወረራ በቆየባቸው ጊዜያት አሰቃቂ ግፍ ሲፈጽም መቆየቱን ነዋሪዎች ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 10 ቀን…

አሸባሪው የህወሃት ቡድን በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ በሃሙሲት ከተማ በወረራ በቆየባቸው ጊዜያት አሰቃቂ ግፍ ሲፈጽም መቆየቱን ነዋሪዎች ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 10 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው የህወሃት ቡድን በዋድላ ወረዳ ሃሙሲት ከተማ በወረራ በቆየባቸው ጊዜያት ለጀሮ የሚሰቀጥጥ ለማየት የሚዘገንን አሰቃቂ ግፍ ሲፈጽም ቆይታል ሲሉ የከተማው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአሸባሪ ቡድኑ ወራሪ ኃይሎች በከተማዋ ሴቶችን በቡድን አስገድደው በመድፈር፤ሰላማዊ ዜጎችን በጅምላ በመጨፍጨፍና ንብረት በማውደም ግፍ መፈጸማቸውንም ነው ነዋሪዎቹ የገለጹት፡፡ የዋድላ ሃሙሲት ከተማ ነዋሪዎች አሸባሪ ቡድኑ ወደ ከተማዋ ከገባበት እለት ጀምሮ የሰቆቃ ጊዜ እንዳሳለፉ ነው ለመቄት ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የጋዜጠኞች ቡድንም የተናገሩት፡፡ የአሸባሪ ቡድኑ ወራሪ ኃይሎች “በርካታ ወጣቶችን በአደባባይ በግፍ ገድለዋል፤ሴቶችን በቡድን ደፍረዋል፤የግለሰቦችን ቤት በየቀኑ እየፈተሹ ሃብት ንብረት ዘርፈዋል” ነው ያሉት ነዋሪዎቹ፡፡ የዋድላ ሃሙሲት ጤና ጣቢያንና የግብርና ጽ/ቤቱን እና ትምህርት ቤቶችን ዘርፎ ፈርጧል። የሽብር ቡድኑ ሲሽሽ የሃሙሲት ጤና ጣጣቢያን በእሳት ለኩሶት ሂዷል ብለዋል። መቄት ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply