አሸባሪው የህወሓት ቡድን በቆቦ ከተማ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን አውድሟል። አማራ ሚዲያ ማዕከል ታህሳስ 13 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በወረራ…

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በቆቦ ከተማ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን አውድሟል። አማራ ሚዲያ ማዕከል ታህሳስ 13 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በወረራ በቆየባት ቆቦ ከተማ የቆቦ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣ የቆቦ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅና የቆቦ ጊራና ሸለቆ ልማት ፕሮግራም ጽህፈት ቤትን ሙሉ በሙሉ አውድሟል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቆቦ ንኡስ ቅርንጫፍ ተዘርፏል፣ የኤቲኤም ማሽንን ጨምሮ የቀሩ ንብረቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል። የሆስፒታሉ ኃላፊ አቶ ሃይማኖት በላይ እንደገለጹት፤ የሽብር ቡድኑ ባደራጀው የባለሙያ ቡድን አማካኝነት የሆስፒታሉ ዕቃዎችና ማሽኖች ተፈትተው ተዘርፈዋል። ከእቃ ግምጃ ቤት የሚፈልጓቸውን መድኃኒቶችና እቃዎችን ጭነዋል፣ የቀረውንም አገልግሎት እንዳይሰጡ አድርገው ስለማውደማቸው ኢፕድ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply