አሸባሪው የህውሃት ቡድን በሴቶች ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ ለመከላከል የግል ሕይወታችን ጉዳይ ሳይገድበን በጦር ግንባር ተሰልፋናል ሲሉ በተከዜ ግንባር የተሰለፉ የቴወድሮስ ብርጌድ ሴት ዘማቾ…

አሸባሪው የህውሃት ቡድን በሴቶች ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ ለመከላከል የግል ሕይወታችን ጉዳይ ሳይገድበን በጦር ግንባር ተሰልፋናል ሲሉ በተከዜ ግንባር የተሰለፉ የቴወድሮስ ብርጌድ ሴት ዘማቾች ገለፁ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 10 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው የህውሃት ቡድን አመራሮች የወልቃይት የማንነት ጥያቄን አነሳስተሻል በሚል ሰበብ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ አሰቃይተውኛል ትላለች ዘማች ጥሩዬ አያሌው፡፡ አሁንም ወረራ በፈፀመባቸው በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በሴቶች ላይ እያደረሰ ያለው ግፍ ከፍተኛ መሆኑን ከተከዜ ግንባር የገለጸችው ዘማች ጥሩዬ አያሌው የቴወድሮስ ብርጌድ አባል ነች። ግፈኛውን እና አሸባሪውን የህወሃት ቡድን ለመፋለምና ለማጥፋትም የወለድኳትን ልጅ ከቤተሰብ አሰጠግቼ ዘመቻለሁ ትላለች፡፡ ምክኒያቱም ሀገሬም ልጀም እኔም ቤተሰቤም በሰላም መኖር የምንችለው አሸባሪው ቡድን ሲጠፋ ነው ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች፡፡ በግንባሩ አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ በቂ ዝግጅት አድርገናል፤ ዘማቹ ግዳጁን ለመወጣት በሙሉ ወኔ ተነሳስቷል ብላለች፡፡ በትግሉ ደስተኛ ነኝ፤ ግዳጀንም በብቃት ለመወጣት ዝግጁ ነኝ ያለችው ዘማች ጥሩዬ በአሸባሪው ቡድን የሚደርስብንን ግፍና በደል ለመከላከል ሴቾች ትግሉን መቀላቀል አለብን ብላለች፡፡ በተከዜ ግንባር ከጠላት ጋር ፊት ለፊት ተፋጣ ሀገርን ከወራሪው ሀይል ለመታደግ በግንባር ያገኘናት ሌላዋ ዘማች ደግሞ ፀዳል ደረበ ትባላለች፡፡ ዘማች ፀዳል የአንድ ልጅ እናት ብትሆንም ሀገር ከሌለ ልጅን በሰላም ማሳደግ አይቻለም፤ ሴቶች በወራሪው እየተደፈሩ፤ ሀገሬን ለመታደግና ልጀን በሰላም ለማሳደግ የምችለው ወራሪውን ሃይል ለመከላከልና እስከመጨረሻው ለማጥፋት ነው ብላለች። አሸባሪው የህወሃት ቡድን ካልጠፋ በሰላም መኖር ስለሌለ አሁን ወንዶችም ሴቶችም ወደ ዘመቻው መቀላቀል እንደሚገባቸው፤ የሰራዊቱ ሞራል ከፍተኛ በመሆኑም በቅርቡ ጠላትን እንደሚያሸንፉ ተናግራለች። ሌላኛዋ በተከዜ ግንባር የቴወድሮስ ብርጌድ አባል የሆነቸው ዘማች ወርቄ መስፍን አሸባሪው የህወሃት ቡድን አማራን አንገት ለማስደፋት ፤ኢትዮጵያን ለማፍረስ እያካሄደ ያለውን ወረራ ለመመከት መንግስት ባቀረበው ጥሪ መሰረት በግንባር ለመፋለም እና የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለማረጋገጥ በሙሉ ወኔ ተዘጋጅታ ትዕዛዝ እየጠበቀች መሆኑን አስታውቃለች፡፡ በተከዜ ግንባር የቴወድሮስ ብርጌድ የፐርሶኔል ኃላፊ አቶ ዋጋዬ በሪሁን ደግሞ በግንባሩ በዘመቻው እየተሳተፉ ያሉ ሴቶች ፆታዊ ችግሮችና የቤተሰብ ጉዳይ ሳያሳስባቸው እያሳዩት ያለው ቁርጠኝነትና የሰነ ልቦና ዝግጅት ከፍተኛ እንደሆነ መታዘባቸውን ገልፀዋል ሲል የዘገበው የጎንደር ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply