You are currently viewing አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በተኮሰው ከባድ መሳሪያ በሐይቅ ከተማ በአንድ ቤት ሰባት ሰዎች ተገድለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ታህሳስ 13 ቀን 2014 ዓ.ም       አዲስ አበባ ሸዋ አ…

አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በተኮሰው ከባድ መሳሪያ በሐይቅ ከተማ በአንድ ቤት ሰባት ሰዎች ተገድለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 13 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አ…

አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በተኮሰው ከባድ መሳሪያ በሐይቅ ከተማ በአንድ ቤት ሰባት ሰዎች ተገድለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 13 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በተኮሰው ከባድ መሳሪያ በሐይቅ ከተማ በአንድ ቤት ውስጥ ተሸሽገው ከነበሩ 16 ንጹሃን ዜጎች መካከል ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ከጥቃቱ የተረፉ እማኞችና የሟች ቤተሰቦች ገልጸዋል። በሐይቅ ከተማ ተሁለደሬ ወረዳ የስድስት አመት ህጻንን ጨምሮ አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በተኮሰው ከባድ መሳሪያ በአንድ ቤት ሰባት ሰዎች መገደላቸውን አራት ቤተሰባቸውን ያጡትና ከስድስት ወራት ልጃቸው ጋር ከጥቃቱ የተረፉት እማኝ ወ/ሮ ዘኒት ሙሀመድ ተናግረዋል። ‹‹ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም በተለያዩ ክፍሎች ውስጥ 16 ሰዎች ተሰብስበን ነበር። ለመውጣትም እያመነታን በነበረበት አጋጣሚ የከባድ መሳሪያ ጥቃት ተሰነዘረ። አብረውን ከነበሩት ውስጥም ሰባቱ ወዲያውኑ ሞቱ››ብለዋል። ቀደም ሲል የአካካቢው ሰው ቀዬውን ለቆ በመሄዱ የሞቱ ሰዎችን አስከሬን ለማንሳት ተቸግረው መሰንበታቸውን አስታውሰዋል ያለው ኢፕድ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply