
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ሃይል ሶስተኛ ዙር ጦርነቱን በራያ በኩል መጀመሩ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 14 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሃይል ከሚያስተዳድራቸው የራያ አካባቢዎች በተጨማሪ ራያ ቆቦ ጀመዶ እና ባይባዎ አካባቢ ገበሬው ላይ ጦርነት ከፍቷል ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር በወልድያ አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም በአዲስ ቅኝ እና ጃሮታም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሃይል አስጠግቷል ብሏል፡፡ ስለሆነም መላው የአማራ ህዝብ በመንግስት በኩል ጦርነቱ ያለቀ ለማስመሰል የሚደረገዉን አማራን ዳግም የማዘናጋት ሴራ ወደጎን በመተው የህልዉና ትግላችንን ማስቀጠል እንዳለብንም ማህበሩ አሳስቧል፡፡ የምስራቅ አማራ ፋኖን የተቀላቀሉ እና በየአካባቢው ያሉ ፋኖዎች ወደ ራያ ግንባር ከተው እንዲገቡ ጥሪ ቀርቧል። የአማራ ወጣቶች ማህበር በወልድያ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳሰፈረው።
Source: Link to the Post