አሸባሪዎቹ ህወሃትና ሸኔ በከሚሴ እና ኮምቦልቻ የግለሰብና የመንግስት ንብረቶችን በተደራጀ መንገድ መዝረፋቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም…

አሸባሪዎቹ ህወሃትና ሸኔ በከሚሴ እና ኮምቦልቻ የግለሰብና የመንግስት ንብረቶችን በተደራጀ መንገድ መዝረፋቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪዎቹ ህወሃት እና ሸኔ በከሚሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች በቆዩባቸው ጊዜያቶች የግለሰብ እና የመንግስት ንብረቶችን በተደራጀ መንገድ መዝረፋቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ፋብሪካዎችን፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን መዝረፋቸውን እና ማውድማቸውን ነው የገለፁት። እንደዚሁም ለሰብአዊ ድጋፍ የተቀመጡ እህሎችም በሽብር ቡድኖቹ ተጭነው መወሰዳቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ከንብረት ዘረፋው በተጨማሪ ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት እንደተፈጸመባቸውም ነው ነዋሪዎቹ የተናገሩት። አሸባሪዎቹ በኮምቦልቻ ከተማ ማንነትን መሰረት በማድረግ ነዋሪዎችን ገድለዋል፤ ዘርፍዋል። በከሚሴም እንዲሁ ብዙ ጥፋት ማድረሳቸውን ገልጸው፥ ቡድኖቹ የኦሮሚያ እና አማራ ክልል ተወላጆችን እርስ በእርስ ለማጋጨት ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ ይህም የሆነው ለረጅም ዓመታት በመተሳሰብ እና በፍቅር የኖርን ህዝቦች በመሆናችን ነው ብለዋል ነዋሪዎቹ፡፡ ዘገባው የኤፍቢሲ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply