አሸባሪ ቡድኖች እንደሆኑ የተገመቱ ሰዎች በከፈቱት ተኩስ በናይጄሪያ 8 የፖሊስ አዛዦች ተገደሉ፡፡በደቡብ ምስራቅ ናይጄሪያ የሚገኙት የኢግቦ ጎሳ አባላት የሆኑት የቢፋራ ሰዎች፣ ይህንን ጥቃት…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/NugNnYVq1btMBJAkPSnUk4iSblOAh1iQ4SZLbTxrzZ0BJHJwPK6rqk8tGwkRwvg4zIvu3ETmESXHIEchovsjVAdG9mzotBZ7mhQfpSVmxC2OZsp6dumuOwBNt-B5BmYCT2wfHvdvzVqCcvZ-fyKRZzxiVOb7_SplqB3l-ZG7p_dK1rvW3NdNkAMQ2-wV7yPTZ0ijYs5kHEQC3Ky1GXYHhQEmJvPVp4PQoU9GGnl5-9Q8-aIkedivppXYLb8ZwQb7_2aJYLn3SkG4dzpsyeg9hT0AvNGaS5awlVSJnhwXgZ7pI7kxWAE5i2iuuIaanjjDHfHll-hvfQgJxtfDkf7UHg.jpg

አሸባሪ ቡድኖች እንደሆኑ የተገመቱ ሰዎች በከፈቱት ተኩስ በናይጄሪያ 8 የፖሊስ አዛዦች ተገደሉ፡፡

በደቡብ ምስራቅ ናይጄሪያ የሚገኙት የኢግቦ ጎሳ አባላት የሆኑት የቢፋራ ሰዎች፣ ይህንን ጥቃት ሳያደርሱ እንዳልቀሩ መጠርጠሩን ፖሊስ አስታዉቋል፡፡
በተከፈተዉ ጥቃትም ቢያንስ 8 የፖሊስ አዛዦች መገደላቸዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ይህ ግድያ 90 ሚሊየን የናይጄሪያ ዜጎች ፕሬዝዳንት ሞሀመድ ቡሀሪን የሚተካ መሪ ለመምረጥ በተመዘገቡበት ማግስት መሆኑ ነገሮችን አወሳስቧቸዋል ነዉ የተባለዉ፡፡

ጥቃቱ የፊታችን ቅዳሜ ለሚካሄደዉ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሚወጡ ዜጎችን ደህንነት የሚጠብቁ የፖሊስ አባላት ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል መባሉንም አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ
የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply