አሸባሪ ኦነጋዊያን በወረጃርሶ ወረዳ ሸንኮራ ሸሸንግ ላይ አንድ አዕምሮ ህመምተኛን በመግደል አንዲት እናትን አግተው ወደ ጫካ ወሰዱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 3 ቀን 2015 ዓ…

አሸባሪ ኦነጋዊያን በወረጃርሶ ወረዳ ሸንኮራ ሸሸንግ ላይ አንድ አዕምሮ ህመምተኛን በመግደል አንዲት እናትን አግተው ወደ ጫካ ወሰዱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 3 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪ ኦነጋዊያን በወረጃርሶ ወረዳ ሸንኮራ ሸሸንግ ላይ አንድ አዕምሮ ህመምተኛን በመግደል አንዲት እናትን አግተው ወደ ጫካ የወሰዱ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል። ወራሪ ቡድኑ ጥር 1/2015 በፈጸመው እገታ ጉሬዛው ተሾመ የተባለን የአዕምሮ ህመምተኛ አማራ በመሆኑ ብቻ ገድሏል፤ አንዲት የ3 ልጆች እናትንም አግቶ ወደ ጫካ ወስዷል። በተመሳሳይ በወረጃርሶ ትምህርት ቤቱን ወደ ማሰልጠኛ ካምፕነት በቀየረው በሀሮ ገሊላ ቀበሌ ሀሮ ሚካኤል አካባቢ ከ10 በላይ አማራዎችን ከሳምንታት በፊት አግቶ መውሰዱ ይታወቃል። በአባይ ወንዝ ዙሪያ ፍልቅልቅ አካባቢም የጥምቀት በዓል ወግ እና ባህሉ በተጠበቀ መልኩ እንዳይከበርም ከፍተኛ የሆነ መንግስታዊ ጫና እየተደረገ መሆኑ ተገልጧል። በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ክ/ከተማ ቱሉኤጀርሳ አካባቢም አረንጓዴ፣ቢጫ፣ቀይ እና የነገስታት ምስል ያለበት ቲሸርት እንዳይለበስ እና አታሚዎችን ጭምር ለመያዝ ትኩረት ተደርጎ ለመስራት በወረዳ ደረጃ ስምምነት መደረሱን ምንጮች ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply