
አሸናፊ አካሉ እስካሁን ድረስ ፍ/ቤት አለመቅረቡ የፍትህ ሂደቱ አሳሳቢ ደረጃ ለመድረሱ አመላካች ነው ሲሉ ቤተሰቦች ቅሬታ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸናፊ አካሉ እስካሁን ድረስ ፍ/ቤት አለመቅረቡ የፍትህ ሂደቱ አሳሳቢ ደረጃ ለመድረሱ አመላካች ነው የሚሉት ቤተሰቦቹ መንግስታዊ መዋቅር ዘርግቶ ከጫካ የአፈና መንገድ በባሰ መልኩ መሀል ከተማ ላይ ሆኖ እየፈጸመ ያለ መንግስታዊ መዋቅር መኖሩ በእርግጥም አሳሳቢ ጊዜ ላይ ስለመድረሳችን ማሳያ ነው ብለውታል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ያነጋገራቸው ምንጮች እንደሚሉት አሸናፊ አካሉ ከጥር 7/2015 ጀምሮ በመንግስታዊ መዋቅር አፈና ተፈጽሚበታል። በአድማ ብተና አማካኝነት ባህር ዳር ከመኖሪያ ቤቱ የአፈና እስር የተፈጸመበት የአብን አመራር አሸናፊ አካሉ አድራሻው በትክክል ባለመነገሩ ቤተሰብ በከፍተኛ ጭንቀት ላይ መክረሙ ይታወቃል። ይህ ብቻ ሳይሆን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ ፍ/ቤትም እንዲቀርብ አልተደረገም። በቤተሰብ በኩል አካልን ነጻ የማውጣት አቤቱታ ለባህር ዳር ወረዳ ፍ/ቤት እና ለባህር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት በተወካይ በኩል መቅረቡ ይታወቃል። ይህን ተከትሎም የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለማክሰኞ ጥር 16/2015 ምላሹን ይዞ እንዲቀርብ በባህር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት መታዘዙ ይታወሳል።
Source: Link to the Post