አሸዋ ሲጭንና ሲያወርድ የነበረ ወጣት ተሽከርካሪው ከህንጻው ጋር አጣብቆት ህይወቱ አለፈ።በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት ሚሊኒየም ጀርባ አሻዋ የጫነው መኪና የሰራተኛውን ህይወት ነጥቋል።የተሽ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/ibBwgmdjGiacNBKsaWQ1BwUPQt9NWJcJ4Ydy6Fveyaq-lATGRfZh5Z6PBk_c5rQxwMsAslSA-zmbA5W55ojLVCAdtoMVHG6S_1utuHDOtJqVvtyJcWPTbTghq2ZW1IPLdCDwTkRRMyybyccwSuYF49PPqE1vUGRNonDkB8TBsFup-h5Wh3Hinf17JczwNl2JdRp4SJdHKFrpBUHhltilQ-ORNyhQNrguotwulI6C9HtLWDCqvfJsSY9ctcvuORIlXGXGuOkadZMSL88cdlDQ4WMY-6Iabt8SWDSJKU4eX7HdPkhVEEVjtLnQlhU1yYz5ZydOQx4UtcLqBQjDiIZH8Q.jpg

አሸዋ ሲጭንና ሲያወርድ የነበረ ወጣት ተሽከርካሪው ከህንጻው ጋር አጣብቆት ህይወቱ አለፈ።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት ሚሊኒየም ጀርባ አሻዋ የጫነው መኪና የሰራተኛውን ህይወት ነጥቋል።

የተሽከርካሪው የኋላ በር አለመዘጋቱን ያላወቀው ይህ ሰራተኛ መኪናው በድንገት በሚንቀሳቀስበት ወቅት የኋለ በሩ ተከፍቶ ሰራተኛው አንገቱን ከህጻው ጋር አጋጭቶት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል።

አደጋውን ያደረሰው አሽከርካሪ እጁን ለፖሊስ ወዲያውኑ ሰጥቷል።

የቀን ሰራተኛው ህይወቱ ወዲያውኑ መለፋን ኢትዮ ኤፍ ኤም አረጋግጧል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ የሟቹን አስክሬን ከቦታው አንስቶ ለተጨማሪ ምርመራ ሆስፒታል ወስዶታል።

አሽከርካሪዎች የጭነት አገልግሎት በሚሰጡበት ጊዜ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ፖሊስ መልክቱን አስተላልፏል።

በሔኖክ ወ/ ገብርኤል

ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply