
– “ስማርት ሶሉሽን ለስማርት ኢንቨስተሮች” የተሰኘ ፕሮጀክት አስተዋወቀ
አዋሽ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ፤ “ስማርት ሶሉሽን ለስማርት ኢንቨስተሮች” በሚል ከዛሬ ነሃሴ 20 ቀን 2015 እስከ ህዳር 16 ቀን 2016 ዓ.ም የሚዘልቅ ልዩ አክሲዮን ሽያጭ መጀመሩን አስታወቀ።
የአሸዋ ቴክሎጂ ሶሉሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል በቀለ፣ ከትላንት በስቲያ ሐሙስ ጉዳዩን አስመልክቶ በሳፋየር አዲስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
“ስማርት ሶሉሽን ለስማርት ኢንቨስተሮች” በሚል መርህ ለኢትዮጵያውያንና ለትውልደ ኢትዮጵያውያ ልዩ የኢንቨስትመንት ጥቅም የሚያስገኝ ዕድል ይዘን መጥተናል ብለዋል- ዋና ስራ አስኪያጁ በጋዜጣዊ መግለጫው።
ፕሮጀክቱን በአገር ውስጥ ለመተግበር ከ112,000,000 ብር በላይ ኢንቨስትመንት የሚፈጅ መሆኑን የጠቆሙት ሥራ አስኪያጁ፤ ይኼ ኢንቨስትመንት በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ውስጥ በየዓመቱ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ የሚያስገኝ ነው ብለዋል።
“ድርጅታችን ሲቋቋም ከሚያስፈልገው የ200 ሚሊዮን ብር አክሲዮን ወደ 2 ቢሊዮን ብር ከፍ እንዲል ቦርዱ በወሰነው መሰረት ቀሪ አክሲዮኖቻችን በአጭር ጊዜ ሸጦ ለመጨረስ የተለያዩ ፓኬጆችን በማውጣት እየሰራ ነው።” ሲሉም አክለዋል- አቶ ዳንኤል።
በዚህም መሰረት፣ ድርጅቱ የአሸዋ ስማርት (ERP)፡- የሰው ሃብት አስተዳደር፣ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ፣ ኢንዱስትሪና የመሳሰሉትን የቢዝነስ ክንውኖችን የሚያቀላጥፍ፤ የተቋማትን ወጪ የሚቀንስ፣ ትርፋማነትን የሚጨምርና፣ ቀልጣፋ የአሰራር ሂደትን የሚፈጥር- ሁሉንም በአንድ ላይ የያዘ- ከ13 በላይ ኢንዱስትሪዎችን የሚሸፍን አስተማማኝ ሶፍትዌር በሳስ እና በሽያጭ መልክ ለገበያ አቅርቧል።
“Smart website Builder” የተሰኘው የድረ-ገጽ መገንቢያችን በደቂቃዎች ውስጥ ድንቅ ድረ-ገፃችን ለመፍጠር ያስችላል” ብሏል-ድርጅቱ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ።
የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ በሰጡት ማብራሪያ፤ “እነዚህ የስማርት ፕሮጀክት አካል ላይ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን ለማህበረሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ በፕሮጀክቱ ውስጥ በሚሰሩ ሥራዎች ላይ ልዩ ጥቅም የሚያስገኘውን አክሲዮን የሚገዙ ኢንቨስተሮች ለተከታታይ አራት ዓመት ከሚገኘው ትርፍ በየዓመቱ የ50% ተጠቃሚ ይሆናሉ” ብለዋል።
“አንድ ኢንቨስተር በ500ሺ ብር አክሲዮን ሲገዛ በአጠቃላይ በድምሩ 6,910,762.25 የሚያገኝ ሲሆን ከ4 ዓመት በኋላ መደበኛ ባለአክሲዮን በመሆን የጠቅላላ ትርፍ ተካፋይ ይሆናል።” ሲሉ አስረድተዋል- ዋና ሥራ አስኪያጁ።
አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን፤ ቴክኖሎጂን ዲሞክራሲያዊ በማድረግ ለማህበረሰቡ ዘመኑን የዋጁ ድንቅ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በማቅረብ፣ በአገራችን ያለውን ዘልማዳዊ የቢዝነስ ሂደት በመቀየር፤ ቢዝነስን ቀላል፣ ዘመናዊና አስተማማኝ ለማድረግ አልሞ የሚንቀሳቀስ ድርጅት መሆኑ ታውቋል።
Source: Link to the Post