አሻራ መረጃ (ታህሳስ 26፣ 2013ዓ.ም) 1) በአቶ በላይነህ ክንዴ ከ4.5 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ  ውጭ የተገነባው የዘይት ፋብሪካ ወደ አገልግሎት ገባ፡፡ ፋብሪካው  የውጭ ምንዛሬን የሚ…

አሻራ መረጃ (ታህሳስ 26፣ 2013ዓ.ም) 1) በአቶ በላይነህ ክንዴ ከ4.5 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ውጭ የተገነባው የዘይት ፋብሪካ ወደ አገልግሎት ገባ፡፡ ፋብሪካው የውጭ ምንዛሬን የሚ…

አሻራ መረጃ (ታህሳስ 26፣ 2013ዓ.ም) 1) በአቶ በላይነህ ክንዴ ከ4.5 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ውጭ የተገነባው የዘይት ፋብሪካ ወደ አገልግሎት ገባ፡፡ ፋብሪካው የውጭ ምንዛሬን የሚያስቀር እና ወደ ውጭ መላክን የሚያበረታታ ነው፡፡ በስሩም ሰባት የሚደርሱ ፋብሪካዎችን ያካተተ ሲሆን የሳሙና እና የፕላቲስቲክ ፋብሪካዎቹ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በፌቨላ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስር የሚተዳደረው ይህ የዘይት ፋብሪካ ሀገሪቱ ካላት ጥቅል የዘይት ፍላጎት ከ60 ከመቶ በላዮን የመሸፈን አቅም ሲኖረው፣ ሀገሪቱ በየዓመቱ ለዘይት የምታወጣውን 460 ሚሊየን ዶላር ወጪ የሚያስቀር እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በአንድ ወቅት በቲውተር ገፃቸው ፅፈው ነበር፡፡… ይህ ሆኖ እያለ አንዳንድ ሚዲያዎች የዚህን ግዙፍ ፋብሪካ የግንባታ ወጪ 990 ሚሊየን ብለው ያወጡት ዘገባ ፍፁም የተሳሳተ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ በ30 ሄክታር መሬት ላይ ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ከተማ ላይ ያረፈው ይህ ፋብሪካ ለ 4ሺ ሰዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የስራ ዕድል ይፈጥራል፡፡ ለአርሶአደሩም በኩታገጠም እያመረ እሴት ጨምሮ እንዲሸጥ የሚያበረታታ ሲሆን፣ በዚህ ፕሮጀክት በርካታ አርሶአደሮች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ የብድር አቅርቦት እና የመብራት አገልግሎት አለመሟላት የፕሮጀክቱ ፈተና የነበረ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ይሄን ሁሉ ተቋቁሞ አልፎ ለምርት ደርሷል፡፡ ዋጋው እንደተተመነም በመላው ሀገሪቱ እና በአጎራባች ሀገራት መሰራጨት ይጀምራል፡፡ የዘይት ፋብሪካው በአፍሪካ የመጀመሪያው ግዙፍ ፋብሪካ ሲሆን፣ ወደ ውጭ የሚገባን ዘይት ተኪ እና የሚወጣን ደግሞ እሴት ጨምሮ እንዲወጣ የሚያደርግ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ የግብርናን ክፍለ ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ ለሚደረገው ሽግግር አይን ገላጭ ሲሆን፣ ለተፈጥሮ ሳይንስ ምሩቃንም ልዮ የጥናት ማዕከል ሆኖ ያገለግላል፡፡፡ የቴክኒክ ግንባታው በቻይና ኢንጂነሮች የተሰራ ሲሆን ወደ ሀገር ውስጥ የእውቀት ሽግግር እንዲኖር ከ900 በላይ የኬሚካል፣የኢንዱስትሪ፣ የኤሌክትሪካል፣ የቴክስታይል ኢንጅነሮች ስልጠና ወስደው ወደ ተግባር ገብተዋል፡፡ 2) በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በትናንትናው ዕለት ሁለት ሰዎች ግልገል በለስ አቅራቢያ በጣታቂዎች ተገለዋል፡፡ አንድ ካህን ወዲያው በጥይት ሲገደሉ አካላቸውን ሳይቀር ታጣቂዎች ግፍ ፈፅመውበታል፡፡ ሁለተኛው ሆስፒታል ላይ ያረፈ ሲሆን አንደኛው በፀና የቆሰለው ህክምና ክትትል ላይ ይገኛል፡፡ በድባጤ ወረዳም የታጣቂዎች እንቅስቃሴ በመኖሩ ስጋቱ አገርሽቷል፡፡ በአቶ ተስፈየ ቤልጂጌ የሚመራው ኮማንድ ፓስት ከባለፈው አንፃራዊ ሰላምን ቢያረጋግጥም፣ መሰረታዊ ለውጥ ግን አላመጣም፡፡ አቶ ተስፋየ ቤልጅጌ ለሄደ ለመጣው አዳሪ እና ያሸነፈ መስሎ ለታያቸው ሁሉ ተንበርካኪ ስለሆኑ ቁርጠኛ አቋም ይዘው ላይሰሩ ይችላሉ የሚሏቸው አሉ፡፡ ኮማንድ ፓስቱ ስራ ከጀመረ ወዲህ 50 ሺ የሚደርሱ ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን በአጠቃላይ ከመተከል ህዝብ 70 ከመቶው አካባቢ ተፈናቅሏል፡፡ የተፈናቀለው በቁጥር ሲሰላ 170ሺ አካባቢ የደረሰ ሲሆን ፣እርዳታውም በተገቢው ሁኔታ እየደረሰ አይደለም፡፡ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ረዳሁት ያለው 8 ሚሊየን ብር ትራንስፓርት የለም በሚል ሰበብ አሶሳ ላይ መራገፉም ቅሬታን ፈጥሯል፡፡ ታጣቂዎች የቡድን መሳሪያ የታጠቁ ሲሆን፣ የመድሃኒት አገልግሎት የሚሰጥ የህክምና ቡድንም አላቸው፡፡ የደንብ ልብሳቸውም በብዛት የአማራ ወይም የቢሻንጉል ልዮ ሀይል ልብስ ነው፡፡ ትጥቅ እና ስንቅ፣መረጃ እና የጦር ልምምድ በመንግስት መዋቅር እንደሚሰጣቸው የታወቀ ሲሆን፣መንግስታዊ ሽብር በመሆኑ ጉዳዮ ፈጣን እልባት አጥቷል፡፡ በመተከል ያለው ፍላጎት በሀገር ውስጥ በኦነግ ተስፋፊነት ፣ከሀገር ውጭ ደግሞ በነግብፅ ሴራ የሚዘወር ሲሆን ሱዳን 30ኪሜትር ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቃ ከገባች በኃላ በህዳሴ ግድብ ለመደራደር ፈቃደኛ ሆናለች፡፡ ሱዳን በአፍሪካ አጥኝዎች የቀረበውን ሀሳብ አልቀበልም ብላለች፡፡ ሱዳን ግን በቢሻንጉል እና በአማራ ክልሎች በኩል ድንበሯን እያሰፋች ለመደራደር ፈቅዳለች፡፡ ሱዳን ከዓባይ ግድብ ይልቅ የድንበር ጉዳይ ያሳስባታል፡፡ ምናልባትም በ30 ኪሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን የዓባይ ግድብን ግዛቴ ነው ብየ እጠቀልለዋለሁ ብላ ሳታልም አትቀርም፡፡ ኢትዮጵያ በድንበሩ ጉዳይ እስካሁን መለሳለስን ያሳየች ሲሆን ሱዳን ግን የክፍለዘመኗ ስኬት አድርጋ እየተናገረች ነው፡፡ 3)የሰላም ሚኒስቴር ለ35 ሺ ወጣቶች ስለ ሰላም እና ሀገራዊ አንድነት ስልጠና ሊሰጥ መሆኑ እያስተቸው ነው፡፡ የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ከ50 ሺ በላይ ከትግራይ ተወላጆች፣ 40 ሺ አካባቢ ከወላይታ ተወላጆችን በድምሩ ከ90 ሺ እስከ 100ሺ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተቀንሰዋል፡፡ የኦሮሚያ የፀጥታ ሀይል የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት በቁጥር በአስር እጥፍ ይበልጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ መካላከያ ሰራዊት አልጀዚራ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ከ100 ሺ እስከ 180 ሺ ብቻ ነው፡፡ ይህም ከኤርትራ መካላከያ ሰራዊት ቁጥር ያንሳል፡፡ ከየክልሎች የፀጥታ ሀይልም ያንሳል፡፡ የፌዴራል መንግስቱ በተረኝነት መንፈስ በተጓደሉ የመካላከያ ሰራዊት ከአንድ ብሄር ብቻ ለመተካት እነ አባዱላ ገመዳ እየሰሩ ነው፡፡ መካላከያ እንደ ህወኃት ዘመን በአንድ አካባቢ ብቻ ከተሞላ የክልል ልዮ ሀይል ይጠፋና መካላከያው በኢትዮጵያ ስም የአንድ ብሄር ብቻ ይሆናል፡፡ የደህንነት መዋቅሩም ከአማራ እና ከትግራይ ክልል ውጭ በነ አባዱላ ወገኖች ብቻ የታዘ ሲሆን፣ የፍትህ ተቋሙም ተመሳሳይ ነው፡፡ የብሄራዊ ደህንነት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከላይ ቢቀመጡም የሀገር ውስጥ ደህንነት መመሪያዎች፣የክልሎች ደህንነት የቢሻንጉልን ጉምዝ ጨምሮ በአንድ አካባቢ ሰዎች የታዘ ነው፡፡ ንግድ ባንክ፣ መብራት ሀይል፣ አየር መንገድ እና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳድርም በተመሳሳይ የተረኝነት ወረራ የተፈፀመባቸው ተቋማት ናቸው፡፡ ተቋማት ዘረኛ እና አግላይ በሆኑበት ሁኔታ እንኳን 35 ሺ ህዝብ 100 ሚሊየኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ስልጠና ቢሰጠው ሰላም አይረጋገጥም፡፡ የኢህአዴግ ርዝራዥ የወጣቶች ሊጎችን አሰልጥኖ እና ሰብኮ የሚፈናቀለውን እና የሚጨፈጨፈውን ማዳን ፈፅሞ ማዳን አይቻልም፡፡ ሀገሪቱ ግጭት እና የጅምላ ግድያ ስጋት በቀጣይ እንዳለባት የኢትዮጵያ ሰባዊ መብት ኮሚሽን እያሳሰበ ባለበት ሁኔታ ለሚዲያ ፍጆታ ብቻ ስልጠና መባሉ የአብይ አህመድ ችግር አቅላይ ሆኖ ችግር የሚያከብድ መሆኑን ያስረግጣል፡፡ ተቋማትን ማጠናከር፣ የህግ የበላይነትን ማስከበር፣ ሀገራዊ አንድነትን በፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንጂ ማምጣት የሚቻለው በስብሰባ ወግ አይደለም፡፡ችግርን አቅሎ መመልከት እና ቀድሞ በበቂ ትንተና ተዘጋጅቶ አለመቆም የለውጡ መንግስት ሁነኛ ድክመት ተደርጎም ይወሰዳል፡፡ https://m.youtube.com/channel/UCsfBw4xrhJzdMTzhWk_uX2A…

Source: Link to the Post

Leave a Reply