You are currently viewing አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ የአማራ ወጣቶች ማህበር የአማራ ህዝብ የሚታገልላቸው አላማዎች በሚል በሚያወጣዎች ተከታታይ ጽሑፎች አምስተኛውን እንደሚከተለው አቅርቧል የአማራ ህዝብ ብሎም የአማራ…

አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ የአማራ ወጣቶች ማህበር የአማራ ህዝብ የሚታገልላቸው አላማዎች በሚል በሚያወጣዎች ተከታታይ ጽሑፎች አምስተኛውን እንደሚከተለው አቅርቧል የአማራ ህዝብ ብሎም የአማራ…

አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ የአማራ ወጣቶች ማህበር የአማራ ህዝብ የሚታገልላቸው አላማዎች በሚል በሚያወጣዎች ተከታታይ ጽሑፎች አምስተኛውን እንደሚከተለው አቅርቧል የአማራ ህዝብ ብሎም የአማራ ወጣቶች የምንታገልለት ዓላማ አምስት( 5) ፦የዘውግ ፌደራሊዝሙ ያስከተላቸው የግዛት ወሰንና የማንነት ጥያቄዎችን እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ የእርምት እርምጃ መውሰድ ‼️ የህውሃት ኢሃዴግ የሃገራችን ፌደራሊዝም አከላለል በዋናነት ዘውግን ማዕከል ያደረገ ነው ።በዚህ የአካላለል ሂደት ወደ አንድ የዘውግ ክልል ለመካለል በዋናነት የሚታየው የህዝቦች ዘውጋዊ ማንነት ነው ።በዚህም ሳቢያ የሃገራችን አብዛኛው ክልሎች መጠሪያቸውን የሚያገኙት ለክልሉ መከለያነት እንደ ዋነኛ መስፈርት በሚያገለግለው የዘውግ ስም ነው ።ሆኖም የሃገሪቱ አብዛኛው ክልሎች ከተዋቀሩበት ከዚህ እሳቤ ባፈነገጠ መንገድ በወልቃይት ፣ሁመራ ፣ራያ ፣መተከል ፣ደራ ወዘተ አካባቢዎች የአማራ ዘውጋዊ ማንነት ያላቸው በርካታ ቁጥር ያላቸው ህዝቦች ማንነታቸውን በማይገልፅ ክልል ውስጥ እንዲካለል በመደረጉ ሳቢያ በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ፣ማንነት ተኮር የዘር ማጥፋት ፥ማፅዳት ፣ሀብት ንብረት ውድመት እና ማፈናቀል በከፍተኛ ሁኔታ በአማራ ህዝብ ላይ ተፈፅሟል ።እየተፈፀመም ይገኛል ። መተከል ፣ወልቃይት እና ራያ ወደ ሌላ ክልሎች እንዲሄዱ የተደረገበት የተለያየ ምክንያት አለ ።እነዚህም ፦ 1). እነዚህን ክልሎች በፊታውራሪነት ያካለለው አማራ ጠሉ የዘውግ ፓለቲካ ጨቋኝ የሚለውን የአማራ ዘውግ በሁሉም መስክ በማዳከም አከርካሪውን መምታት እንዳለበት አጥብቆ የሚያምን ነው ።በመሆኑም ጨቋኝ የተባለው የአማራ ዘውግ ሰፊ ክልል እንዳይዝ ለማድረግ ነው ። 2).እነዚህ ቦታዎች ለም መሬት በመሆናቸው መልክዓ ምድራዊ አቀማመጣቸው በወቅቱ ፓለቲካ ሲዘውር የነበረው ልሂቅ ዋነኛ መሰረት ወደ ሆነችው ትግራይ እንዲጠቃለሉ በአማራ ህዝብ ኪሳራ የትግራይን ኢኮኖሚ እንዲያጎለብቱ ተደርጓል ።በወልቃይትና ራያ ለም መሬቶች ከእሩብ ክፍለዘመን በላይ እነዚህ አማራ ጠል ሀይሎች ተጠቃሚ ሆነው እንደነበር የሚታወስ ነው ። 3).መልክዓ ምድራዊ አቀማመጡ ወደ ትግራይ ለማካለል ያልተመቸው ሌላው ለም ቦታ ፣የጎጃም ጠቅላይ ግዛትን መተከል ደግሞ ከአማራ ተነጥቆ የትግራይ ልሂቅ እንደ ሁለተኛ ክልል ያዩት በነበረው ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስር ተካልሎ በኢንቨስትመንት ስም ወደ ቦታው ለሚያቀኑ የስርዓቱ ታማኞች ንብርት እንዲሆን ተደርጎ ነበር ።አሁንም የአገዛዝ ለውጥ ተደርጎ በተመሳሳይ የአገዛዙ ብሄር ተወላጆች መጠቀሚያ ሆኖ ይገኛል ። 4).ሌላው የአማራ ህዝብ የማንነት ጥያቄ የሚያነሳበት ቦታ ደራ ነው ።ይህ ቦታ ከፍተኛ የሆነ ሰፋፊ ለም መሬት የሚገኝበት ከመሆኑም ባሻገር ከፍተኛ የሆነ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ከአማራ ክልል እንዲወጣ ተደርጓል ። እነዚህ ቦታዎች ከአማራ ክልል መነጠቃቸው ለክልሉ ህዝብ ከኢኮኖሚያዊና ስትራቴጂካዊ ጉዳታቸው ባላነሰ ሁኔታ ከማንነት እና ባህል ጋር የተያያዙ በርካታ ጉዳቶች አምጥተዋል ።በእነዚህ ቦታዎች የሚገኙ የአማራ ተወላጆች ከዕለታት አንድ ቀን የአማራ ማንነት ጥያቄ ያነሳሉ በሚል የዘር ማጥፋት ፥የዘር ማፅዳት ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል ፣ሃገር ለቀው እንዲሰደዱ የሚያደርጉ በደሎች አስተናግደዋል ፣ከሞትና መሰደድ የተረፉት ደግሞ በቋንቋቸው እንዳይማሩ ፣ባህላቸውን እንዲያጡ እንዲሁም ማንነታቸውን በሀይል እንዲቀይሩ ተደርጓል ። ይህ ሁሉ ማንነት እና ባህልን ለማጥፋት የተደረገ ወንጀል ከመሬትና ግዛት መካለል በላይ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጥያቄ ይዞ የሚመጣ ነው ።በሃገራችን ከታዩ አሰቃቂ ወንጀሎች ወስጥ በቅርቡ በመተከል የታየው የሰውን ልጅ እንደ ቆሻሻ በስካቫተር ዝቆ ግሬደር የመቅበር እጅግ መራር በደል የታየው በመተከል ነው ። በወልቃይትና ራያ የነበረው ጉዳይ በአማራ ህዝብ ከፍተኛ የደም መስዕዋትነት እርስቶቻችን ወደ ነበሩበት አፅመ እርስታቸው ተመልሰዋል ።ባህሉን ፣ቋንቋውን እና ሁለንተና ማንነቱን ተነጥቆ የነበረው ህዝባችን ወደ ትክክለኛ ማንነቱ በአሁኑ ወቅት የተመለሰ ቢሆን ሃገሪቱን እየገዛ ያለው ስርዓት እቅዱና ፍላጎቱ ግልፅ አይደለም ።የጥያቄው ባለቤት ፣ ባለ ጉዳዩን የአማራ ህዝብን ባገለለ ሁኔታ ከሌሎች ሀይሎች ጋር በመሆን በወልቃይትና ራያ ጉዳይ ድርድር አድርገዋል ።የአማራ ህዝብ በእውነተኛ ልጆቹ ባልተወከለበት ፣ሃሳብና በፍላጎቱን ባልገለፀበት ሁኔታ የተደረገ ድርድር ወይም ስምምነት የሚመጣ መፍትሄ እንደሌለ መላው የአማራ ታጋይ ሀይሎች የምንረዳ ጉዳይ ነው ። በመሆኑም ከላይ በጥቂቱ የተጠቀሱ በአማራ ህዝብ ላይ የደረሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፣በደልና ግፍ በዘላቂነት ለመፍታት የአማራ ታጋይ ሀይሎች የሚከተለውን ማድረግ ይጠበቃል ። 1ኛ).ከአማራ ህዝብ በግፍ የተነጠቁ ሁሉም አፅመ እርስቶች ላይ የሰፈሩ ከህዝቦች አማራ ሆነው ሳለ ወደ ሌላ ክልል የተካለሉበት አካሄድ ስህተት በመሆኑ የዘውግ ፌደራሊዝም በስራ ላይ እስካለ ድረስ እነዚህ ቦታዎች ወደ አማራ ክልል መካለል አለባቸው ። 2ኛ).ከላይ በተጠቀሱ ቦታዎች የተደረጉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፣የዘር ማጥፋት /ማፅዳት ወንጀል የፈፀሙ ሰዎች ወይም ቡድኖች ተጣርተው ተገቢው ቅጣት ማግኘት አለባቸው ።በተጨማሪም ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖቻችን መካስ አለባቸው ። ላንጨርስ የጀመርነው ትግል የለም ።አማራ በቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ ታሪኩን ያድሳል‼️

Source: Link to the Post

Leave a Reply