አሻራ ማስታወሻ (ጥር 13፣ 2013 ዓ.ም) ዛሬ የምክርቤት አባላት ከብዙ መሽኮርመም በኃላ ያነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች በትክክልም የችግሩን መጠን የሚያመላክቱ ናቸው፡፡ 1) የመተከል ጭፍጨፋ…

አሻራ ማስታወሻ (ጥር 13፣ 2013 ዓ.ም) ዛሬ የምክርቤት አባላት ከብዙ መሽኮርመም በኃላ ያነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች በትክክልም የችግሩን መጠን የሚያመላክቱ ናቸው፡፡ 1) የመተከል ጭፍጨፋ…

አሻራ ማስታወሻ (ጥር 13፣ 2013 ዓ.ም) ዛሬ የምክርቤት አባላት ከብዙ መሽኮርመም በኃላ ያነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች በትክክልም የችግሩን መጠን የሚያመላክቱ ናቸው፡፡ 1) የመተከል ጭፍጨፋ የሚመራው ከርዕሰመስተዳድሩ እስከ ቀበሌ ባሉ አመራሮች ቸልተኝነት፣ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንደሆነ አንስተዋል፡፡ በአጠቃላይ በድምዳሜያቸው ደግሞ የመተከል ጭፍጨፋ የተመራው በውስን የመንግስት አካላት ነው የሚለው ሀሳብ ፀንቷል፡፡ 2) ጭፍጨፋው ማንነት ተኮር ነው የሚለው ላይ መግባባት ተደርሷል፡፡ በግፍ የተጨፈጨፉት አማራዎች/ አገዎች ናቸው፡፡ ሂደቱም ዘር ማጥፋት(genocide) እና ዘርን ማጥራት (ethnic cleasing) እንደሆነ በገደምዳሜውም ቢሆን ስምምነት ተደርሶበታል፡፡ ከ200 ሺ በላይ ሲፈናቀሉ፣ ከ600 በላይ በአንድ ወር ብቻ በግፍ ተጨፍጭፈዋል፡፡ 3) መፍትሄው የሽፍታ ባህሪ ያለውን መንግስታዊ ውቅር በአስቸኳይ አዋጁ የህግ የበላይነት ማስከበር እና የአስተዳድር ስራዓቱን ማስተካከል ይገባል የሚል የመፍትሄ ሀሳብ ሰጥቷል፡፡ 4) በቢሻንጉል ጉምዝ አማራ እንዳይታጠቅ፣ ዱላ እንኳን እንዳይዝ ይደረጋል፡፡ ይሄ መስተካከል እንዳለበት ምክርቤቱ ምክረሀሳብ አቅርቧል፡፡ 5) ኦነግ ሸኔ እና የቢሻንጉል ጉምዝ ነፃነት ግንባርን በህወኃት መንገድ መደምሰስ የሚል ሀሳብም ቀርቧል፡፡ 6) ችግርን ቀድሞ ተንትኖ ህግ ማስከበር ያልቻለ ተቋም እንዲጠየቅ የሚሉ ሀሳቦች ተነስተዋል፡፡ 7) የችግሩ ምንጭ የተዛባ ትርክት መሆኑም ስምምነት የተደረሰበት ሲሆን፣ የህወኃት አመለካከት የብልፅግናም መመሪያው እንደሆነው አሻራ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ሲዘግብ ቆይቷል፡፡ የችግር ልየታው የምክርቤቱ ጥሩ የሚባል ነው፡፡ አስፈፃሚ አካሉ የምክርቤቱን ምክረሀሳብ ይጠቀምበታል ወይስ አይጠቀምበትም የሚለው ግን ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ አሻራ በተደጋጋሚ የችግሩ ምንጭ ራሱ መንግስት እና መዋቅሩ እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply