አቃቢ ህግ በእነ እስክንድር ነጋ ላይ አሉኝ ያላቸውን ምስክሮች ከጥር 26 ቀን ጀምሮ እንዲያሰማ ሲል የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

አቃቢ ህግ በእነ እስክንድር ነጋ ላይ አሉኝ ያላቸውን ምስክሮች ከጥር 26 ቀን ጀምሮ እንዲያሰማ ሲል የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 5 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ መጋቢት 29 የነበረው ቀጠሮ በእነ አቶ እስክንድር ነጋ፣ስንታየሁ ቸኮል፣አስቴር ስዩምና አስካለ ደምሌ እንዲሁም በጠበቆች ቅሬታ መቅረቡን ተከትሎ በሰበር ለጥር 5 ቀን 2013 ዓ.ም መደረጉ ይታወሳል። በዛሬው ችሎት በርካታ ቁጥር ያላቸው የባልደራስ አባላትና ደጋፊዎች ችሎቱን ለመታደም ተገኝተዋል። ጉዳዩን የሚከታተለው ችሎቱም የአቃቢ ህግ ምስክሮችን የምሰማው ከጥር 26 ጀምሮ እስከ የካቲት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ነው ማለቱን ተከትሎ ከተከሳሾችና ከጠበቆች ቅሬታ ቀርቦበታል። ከጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ጋር ያደረግነው ቆይታ እንዳመለከተው የባልደራስ መኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ ቀጠሮው ከመጋቢት 29 ወደ ጥር 5 በማድረግ ማሻሻላቸውን በአድናቆት እንደሚመለከቱት በመግለፅ አመስግነዋል። ከጥር 26 ጀምሮ እስከ የካቲት 28 ድረስ ምስክር ለማሰማት በሚል ፍ/ቤቱ ያስቀመጠውን የቀጠሮ ጊዜ ግን የተፋጠነ ፍትህ እንዳናገኝና በምርጫ ተወዳድረን ህዝብ እንዳይዳኘን ያደርጋል በሚል ቀጠሮው ይስተካከልልን ብለዋል። የባልደራስ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል በበኩሉ “እኔ አሁንም እደግመዋለሁ እኛ ሰው ገለን አይደለም። ጄኖሳይድም ፈፅመን አይደለም። ህዝብ እንዲራብ እንዲጠማ እናቶች እንዲያለቅሱ አድርገን አይደለም እዚህ የታሰርነው ብሏል። ስንታየሁ ሲቀጥልም ” የታሰርነው ይልቁንስ ህዝብን ስለመገብን ጄኖሳይድ እንዳይከሰት ስለተከላከልን …ለግፉሃን እና ለጭቁኖች የተሻለ ሃሳብ ይዘን ድምፅ ስለሆንን ብቻ ነው። በመሆኑም አሁንም ህዝብ በየቦታው እየታረደ ነው ጄኖሳይድ እየተፈፀመ ነው። ነገ የተሻለ ሃሳብ ለህዝቡ በማቅረብ እና በምርጫ ተወዳድረን አገሪቱ አሁን ከገባችበት አረንቋ ማውጣት እንፈልጋለን። ስለዚህ አሁንም የቀጠሮ ቀን ይሻሻል።” ሲል ጠይቋል። በችሎቱ ለመናገር እድል የተሰጣት አስቴር ስዩም እኔም ከአራት ወራት ቀጠሮ ወደዚህ ዝቅ ስላደረጋችሁት አመሰግናለሁ ብላለች። አስቴር ስትቀጥልም ከዚህ መንግስት የተሻለ ሃሳብ፣ ፖሊሲ እና አገር የማስተዳደር አቅም እንዳላቸውና አቃቤ ህግ ያቀረበው ክስም የፈጠራ መሆኑን ጠቅሳ ቀጠሮው እንዲሻሻል ጠይቃለች። ሌላኛው ፍትህ ፈላጊ የባልደራስ አመራር አስካለ ደምሌም ብዙ ህዝብ ይጠብቀናል፤ አሁንም በዚህ መልኩ የተራብነውን ፍትህ በተፋጠነ ሁኔታ እናገኛለን ብለን ተስፋ አናደርግም። በመሆኑም ምስክር የሚሰማበት ቀን ዝቅ ይበልን ስትል አሳስባለች። የተከሳሾችን ቅሬታ ያዳመጡት ዳኞችም ወደ ቢሮ ሄደው ተመካክረው እንደተመለሱ ምስክር የመስማት ቀጠሮው ጥር 26 የሚለው እንደፀና መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን እስከ የካቲት 26 የሚለው ቀርቶ እስከ አራት ድረስ ማለትም ከጥር 26 ,28, 1, 2 ,3 ,4 በየቀኑ አራት አራት ምስክሮች እየተደመጡ እንዲካሄድ መወሰኑን አስታውቋል። በችሎት ከታደሙ የአዲስ አበባ ወጣቶች መካከልም ቁጥራቸው ከ20 በላይ የሚሆኑ የባልደራስ አባላት፣ ደጋፊዎች፣ ጋዜጠኞችንና ሴቶችን ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ሞክራችኋላ በሚል ከረፋዱ አራት ሰዓት ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ በልደታ ባልቻ ፖሊስ ጣቢያ ተይዘው እንደሚገኙ ተገልጧል። ከባልደራስ ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply