You are currently viewing አቃቢ ህግ በወቅታዊ ችግር ምክንያት በጦር መኮንኖች ላይ ያሉኝን ምስክሮች ለህዳር 28 ለማቅረብ ይቸግረኛል ማለቱን ተከትሎ ለታህሳስ 5 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ህ…

አቃቢ ህግ በወቅታዊ ችግር ምክንያት በጦር መኮንኖች ላይ ያሉኝን ምስክሮች ለህዳር 28 ለማቅረብ ይቸግረኛል ማለቱን ተከትሎ ለታህሳስ 5 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህ…

አቃቢ ህግ በወቅታዊ ችግር ምክንያት በጦር መኮንኖች ላይ ያሉኝን ምስክሮች ለህዳር 28 ለማቅረብ ይቸግረኛል ማለቱን ተከትሎ ለታህሳስ 5 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በባህር ዳር እስር ላይ የሚገኙ የጦር መኮንኖች በሁለት ዙር አቃቢ ህግ ምስክሮችን መከታተላቸው ይታወቃል። በዚህም የተከሳሾች ጠበቃ በሙሉ እንደገለፁት እስካሁን 56 ምስክሮች ተሰምቷል። ጉዳዩን የሚከታተለው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ከህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሶስተኛ ዙር ከአሁን በፊት ያልቀረቡ የአቃቢ ህግ ምስክሮችን እንደሚሰማ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። ይሁን እንጅ አቃቢ ህግ በወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታ ምስክሮች በግዳጅ ቀጠና ላይ የሚገኙ በመሆኑ ለህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ምስክሮችን ማቅረብ አልቻልኩም ማለቱን ተከትሎ ፍ/ቤቱ ለታህሳስ 5 ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ከሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጥራችሀል ተብለው በእስር ላይ ያሉ የጦር መኮንኖችና የልዩ ሀይል አባላትም ፍትህ ዘገየብን ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል። ይሁን እንጅ ከወቅቱ ጋር ተያይዞ አብዛኛው አቃቢ ህግ አሉኝ ያላቸው ምስክሮች የፀጥታ አካላት በመሆናቸው፣በግዳጅ ላይ ናቸው መባሉ አሳማኝ ነውና ቀጠሮውም አጭር ነው በሚል ፍ/ቤቱ ከታህሳስ 5 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ምስክሮችን እንሰማለን ስለማለቱ ጠበቃ በሙሉ ገልፀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply