አበረታች መድሃኒት የተጠቀሙ አትሌቶች ታገዱ

አበረታች መድሃኒት ተጠቅመው በተገኙ ሁለት አትሌቶች ላይ ከ4 እስከ 12 ዓመታት የሚደርስ እገዳ ማስተላለፉን የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት ገለጸ፡፡ሁለቱም አትሌቶች በአበረታች መድሃኒት መጠቀም ተጠርጥረው ለአንድ ዓመት ያህል ታግደው መቆየታታቸውን ጽህፈት ቤቱ አስታውሷል፡፡ ባደረገው ምርመራ አትሌት እዮብ ኃብተስላሴ ጎሳ እ.ኤ.አ የካቲት 02/2020 በታይላንድ በተካሄደው ውድድር (Cathinone) የተባለውን የተከለከለ የስፖርት አበረታች ቅመም መጠቀሙ ተረጋግጧል፡፡ በመሆኑም እ.ኤ.አ ከሚያዝያ 03/2020 ጀምሮ ለተከታታይ አራት (4) አመታት በማንኛውም ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ ቅጣት ጥሎበታል፡፡ በውድድሩ ያገኘው ውጤትና የእውቅና ሽልማትም እንደሚሰረዝ አበረታች መድሃኒት ተቆጣጣሪ ተቋሙ ተናግሯል፡፡

በተመሳሳይ አትሌት ወንድወሰን ከተማ ማሞም Cathinone የተባለውን የተከለከለ የስፖርት አበረታች ቅመም መጠቀሙ በመረጋገጡ እ.ኤ.አ እስከ የካቲት 01/2024 ድረስ በማንኛውም ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ እገዳ ተጥሎበት እንደነበር ጽህፈት ቤቱ አስታውሷል፡፡

አትሌት ወንዶሰን መድሃኒት መጠቀሙን ለማረጋገጥ ምርመራ ሲካሄድበት ያቀረባቸው የተሳሳቱ የሰነድ ማስረጃዎች ለተጨማሪ ቅጣት ዳርገውታል፡፡ አትሌቱ ያቀረባቸው ሰነዶች የሐሰት መሆናቸው በመረጋገጡና በፀረ-ዶፒንግ ህጉ አንቀፅ 2.5 ላይ የተደነገገውን የፀረ-ዶፒንግ እንቅስቃሴውን የማስተጓጎልና አቅጣጫ የማሳት የህግ ጥሰት መፈፀሙ በመረጋገጡ ቀደም ሲል ከተጣለበት የአራት (4) አመት እገዳ ተጨማሪ ስምንት ዓመታት በድምሩ 12 ዓመታት ከስፖርት ተሳትፎ መታገዱን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት በቀጣይም የምርመራና ቁጥጥር ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግሯል፡፡

<p style=”text-align: left;”>ቀን 14/ 03/2013</p>

Source: Link to the Post

Leave a Reply