በጦርነቱ ወቅት የሮማው ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት አቡነ ፒዮስ 12ኛ የናዚን የአይሁዶችን የዘር ማጥፋት (Holocaust) ሙከራ እቅድ እኤአ በ1942 ያውቁ እንደነበር በቫቲካን ቤተመዘክር የተገኘ ደብዳቤ አመለከተ፡፡
ይህ በወቅቱ ስለጉዳዩ ግልጽና በቂ መረጃ አልነበረኝም ከሚለው የቤተክርስቲያኒቱ አቋም ጋር የሚጋጭ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
ለሊቀጳጳሱ የተላከው ደብዳቤው የተጻፈው እኤአ ታህሳስ 14 ቀን 1942 የናዚን ድርጊት ይቃወሙ በነበሩ ጀርመናዊ ካህን ሎተር ኮኒግ መሆኑ በሮይተር ዘገባ ተገልጿል፡፡
ደብዳቤው በእየለቱ ወደ 6ሺ የሚደርሱ ፖላንዳውያን እና አይሁዶች በበልዜክ ማጎሪያ ካምፕ (SS-furnaces” በተባለው ማቃጠያ) ውስጥ ይገደሉ እንደነበር ይገልጻል፡፡
በሊቀጳጳሱ የግል ጸሀፊ በኩል የተላከውን ደብዳቤ ያገኙት የቤተመዘክር ባለሙያ ጂኦቫኒ ኮኮ፣ ቫቲካን ደብዳቤው በወቅቱ በማጎሪያ ካምፖቹ ውስጥ ይካሄዱ ስለነበሩ ግፎችና ግድያዎች በግልጽ ታውቅ እንደነበር ያረጋግጣል ብለዋል፡፡
Source: Link to the Post