አቢሲንያ ባንክ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው ያለውን የዲጂታል ቪዛ ካርድ እና ፈጣን የቪዛ ካርድ ህትመት አገልግሎት ቴክኖሎጂን በዛሬው እለት አስተዋውቋል።በባንኪንግ ኢንደስትሪው በየጊዜው ተለዋ…

አቢሲንያ ባንክ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው ያለውን የዲጂታል ቪዛ ካርድ እና ፈጣን የቪዛ ካርድ ህትመት አገልግሎት ቴክኖሎጂን በዛሬው እለት አስተዋውቋል።

በባንኪንግ ኢንደስትሪው በየጊዜው ተለዋዋጭ የሆነውን የደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት፣ በቴክኖሎጂ እና በሰለጠነ የሰው ኃይል በመታገዝ የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት ይቻል ዘንድ ደምበኞቹ የቪዛ ካርድ ጥያቄያቸውን ወዲያውኑ የሚያገኙበትና ያለ (ATM) ካርድ ገንዘብ ወጪ ማድረግም ሆነ ክፍያዎችን መፈፀም የሚያስችላቸውን የዲጂታል ቪዛ ካርድ አገልግሎት ቴክኖሎጂዎች ነው ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ያስመረቀው፡፡

አቢሲንያ ባንክ እ.አ.አ በሴፕቴምበር 2020 በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን የቨርቹዋል ባንኪንግ አገልግሎት ማዕከሉን ማስመረቁ ለትውስታ ተነስቷል፡፡

ባንኩ በቀጣይ አመታት ይህን አገልግሎት በአዲስ አበባም ሆነ በክልሎች በስፋት ለማዳረስ በዕቅድ የተያዘ ሲሆን፣ ይህንን አገልግሎት በጀሞ፤ ብሄራዊ ሙዝየም፣ ጎፋ እና መሀል ሰሚት በሚገኙት ቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎች ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

አቢሲኒያ ባንክ በዛሬው እለት ያስመረቃቸው የቴክኖሎጂ አይነቶች ለባንኩ ነባር ደምበኞች፣ ፣ካርድ ለጠፋባቸው የምትክ ካርድ አገልግሎት እንዲሁም አዲስ ሂሳብ በቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከል ለሚከፍቱ ወዲያውኑ የቪዛ ካርድ እንዲያገኙ የሚያስችላቸው መሆኑ ተነግሯል።

አገልግሎቱ በቀን ለ 24 ሰዓት በሳምንት ለ 7 ቀናት የሚሰራ መሆኑ እና በካርድ ወዲያውኑ በ ATM እና በPOS ላይ ግብይት መፈፀም መቻሉ አሰራሩን ልዩ ያደርገዋል ተብሏል።

ፈጣን የቪዛ ካርድ ህትመት አገልግሎት የሚባለው የቴክኖሎጂ አይነት የዲጂታል ቪዛ ካርድ አገልግሎት ሲሆን ይህም አገልግሎት ስልካችንን ልክ እንደ (ATM) ካርድ በመጠቀም የ ATM ካርድ ሳይኖረን ገንዘብ ወጭ ማድረግ እና ክፍያዎችን መፈጸም የምንችልበት ቴክኖሎጂ መሆኑን ሰምተናል።

የዲጂታል ቪዛ ካርድ አገልግሎት ለማግኘት ደንበኞች ስልካቸውን እንደ ATM ካርድ መገልገል የሚችሉ ሲሆን የአፖሎ መተግበሪያን በመጠቀም ቪዛ ካርዳቸውን ወደ ዲጂታል ቪዛ ካርድ በመቀየር ገንዘብ ከATM ለማውጣትም ሆነ POS ማሽኖች ላይ ለመክፈል ስልካቸውን ጠጋ በማድረግ መጠቀም እንደሚችሉ ተነግሯል።

በሐመረ ፍሬው
ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply