አቢይ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ነዉ::የዘር ፍጅት እየተከናወነ ከሱ በላይ ተወቃሽም ሆነ ተጠያቂ የለም::በአንደኛ ደረጃ በዘር ፍጅት ወንጀለኛነትም የሚጠዬቀዉ አቢይ እራሱ ነዉ ! ——…

አቢይ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ነዉ::የዘር ፍጅት እየተከናወነ ከሱ በላይ ተወቃሽም ሆነ ተጠያቂ የለም::በአንደኛ ደረጃ በዘር ፍጅት ወንጀለኛነትም የሚጠዬቀዉ አቢይ እራሱ ነዉ ! —————- ሸንቁጥ አየለ ———— በመተከል እና በወለጋ የሚካሄደዉን የአማራ እና የአገዉ ማህበረሰብ የዘር ፍጅት በተመለከተ አቢይን ለምን ትወቅሳላችሁ::አቢይ የሀገሪቱን ችግር ሁሉ በአንዴ ሊያስወግድ አይችልም የሚል ብዙ ምክሮች ከቅን ወዳጆቼ ይደርሱኛል:: እኛ የምናለቅሰዉ ህዝባችን እያለቀ ስለሆነ ነዉ::ብዙዉ ሰዉ የሚያለቅሰዉ ደግሞ እነሱ መንግስታችን የሚሉት አካል ስለተወቀሰባቸዉ ነዉ::… ትናንትና የደረሰኝ የአንድ ወዳጄ ምክር ግን ክሁሉም ሰዎች መልዕክት ልቤን አክሻክሮታል:: ለብዙ አመታ የማከብረዉ ወዳጄ በመልዕክቱ “አቢይ መልካም ሰዉ ይመስለኛል::ሁሉንም የሀገሪቱን ችግሮች በአንዴ እንዲፈታ መጠበቅ የለብን::ስለዚህ እንታገሰዉ::”የሚል ሀሳብ ሰደደልኝ:: እኔም መልሼ “የአንተ ቤተሰብ በዘሩ ምክንያት ቢታረድ አቤት ትላለህ ወይስ እንታገሰዉ ትላለህ?::ቤተሰቤ ተጎዳ እያልክ በአገኘህዉ አጋጣሚ ሁሉ ታለቅሳለህ ወይስ እስኪ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ እስኪመቸዉ ትጠብቃለህ?” ብዬ መጠዬቅ:: ለብዙ ጊዜ የማቀዉ ወዳጄም መልስ ሳይሰጠኝ በዚያዉ ቀረ::ምክንያቱም የጠየቅሁት ጥያቄ ጉዳዩን ወደ እራሱ ቤተሰብ አቅርቤ ነዉና ነገሩን ሸሸዉ:: አቢይ ሁሉንም የሀገሪቱን ችግሮች በአንዴ ይፍታ ያለ የለም::ቢያንስ ግን አሁን እየተከናወነ ያለዉን የዘር ፍጅት የማስቆም ወታደራዊ አቅም አለዉ:: ይሄን የዘር ፍጅት ባለማስቆሙ ደግሞ ተጠያቂዉ አቢይ እንጂ የቤኒሻንጉል ክልላዊ መንግስት ወይም የኦሮሚያ መንግስት ሃላፊነት አይደለም::ሀላፊነቱ የሚጀምረዉ ከአቢይ ነዉ:: በተዋረድ ወደ ክልልሎቹ ቢወርድም ቀዳሚ ተወቃሹም ሆነ ተጠያቂዉ አቢይ ነዉ::አቢይ እራሱን ከተጠያቂነት ለማዳን ከፈለገ የነዚህን ክልል አመራሮች በቀላሉ በመለወጥ ሁኔታዎችን ማስተካከል ይችላል:: ስለሆነም በመተከል እና በወለጋ ለሚከናወነዉ የዘር ጭፍጨፋ በዘር ፍጅት ወንጀለኛነትም የሚጠዬቀዉ አቢይ እራሱ ነዉ:: ብዙ ሰዉ ነገሮችን የሚያያቸዉ የሱ አፍንጫ እስኪነካ ባለዉ ርቀት ብቻ ነዉ::ልክ አሁን ምክር መክሮኝ ጥያቄ ስጠይቀዉ በዚያዉ እንደቀረዉ ወዳጄ ብዙ ሰዉ የሱ ጎጆ ካልተነካች አለሙ ሁሉ ሰላም ነዉ ይልሃል::ልክ እንደ አቢይ እንዲሁም እንደ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ማለት ነዉ::የእነሱ ስልጣንን የሚጋፋዉ ወያኔ እንደተመታ ሲያዉቁ በኦሮሚያ እና በመተከል ሰዉ በጅምላ እያለቀ በአደባባይ ወጥተዉ “አሁን መላ ሀገሪቱ ሰላም ነች” እንዳሉት መሆኑ ነዉ:: ለማንኛዉም ከመለስ ዜናዉ እና ከወያኔ አለመማር ታላቅ ነዉር ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ነዉ::ዛሬ እያስቀመጥከዉ የምትሄደዉ ወንጀል ዞሮ እንደሚያንቅህ ለማወቅ ብዙ ምርምር አይጠብቅም:: ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያ የእግዚአብሄር ሀገር ነዉ::ህዝቡም የእግዚአብሄር ህዝብ ነዉ::የኢትዮጵያዊዉን ደም ማንም በማይጠብቀዉ መልክ የሚበቀልለት እግዚአብሄር እራሱ ነዉ:: የእግዚአብሄርም በቀልም መራራ እና ጥልቅ ነዉ::

Source: Link to the Post

Leave a Reply