አባሃዋ ትሬዲንግ ” ዋን ችፕስ” የተባለ ” ምርትቶችን ለገበያ ማቅረቡን አስታወቀ

በሰበታ ዳለታ አካባቢ በሚገኝ ፋብሪካ ከአንድ  ቢልየን ብር በላይ  መዋዕለ ነዋይ በማፍሰስ  ዋን ቺፕስ የተባለ የምርት  ስም  በበቆሎ እና በድንች የሚሰሩ ዘጠኝ  አይነት የችፕስ  አይነቶችን ማቅረቡን ዛሬ በሀያት ሪጀንሲ ድርጅቱ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።
ድርጅቱ የሚጠቀምባቸው ግብአቶች መሉ ለሙሉ ከውጭ የሚመጡ ሲሆን ለወደፊት  ለምርቱ የሚያስፈልገውን ዘር ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት   ከገበሬዎች ጋር ለመስራት እቅድ እንዳለም ተገልፇል።

አሁን በተጀመረው ምርት  350 ቋሚ ሰራተኞች የስራ እድል አግኝተዋልም ተብሏል።

አባሃዋ ትሬዲንግ የዋን ውሃ አምራች ሲሆን ከተመሰረተ ሀምሳ አመት የሞላው ድርጅት ነው ።

The post አባሃዋ ትሬዲንግ ” ዋን ችፕስ” የተባለ ” ምርትቶችን ለገበያ ማቅረቡን አስታወቀ appeared first on Fidel Post.

Source: Link to the Post

Leave a Reply