You are currently viewing አባ አንዳርጌ አበበ ይባላሉ  የኢህዴን ነባር ታጋይ ፠ በ1979 የአስመራ ዩኒበርስቲ ትምህርታቸውን አቋርጠው  ወደ ሱዳን ወደ ስደት ሲጀምሩ ወደ አሜሪካን ሀገር ሂደው ለመማር ጉጉት የነበራቸ…

አባ አንዳርጌ አበበ ይባላሉ የኢህዴን ነባር ታጋይ ፠ በ1979 የአስመራ ዩኒበርስቲ ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ሱዳን ወደ ስደት ሲጀምሩ ወደ አሜሪካን ሀገር ሂደው ለመማር ጉጉት የነበራቸ…

አባ አንዳርጌ አበበ ይባላሉ የኢህዴን ነባር ታጋይ ፠ በ1979 የአስመራ ዩኒበርስቲ ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ሱዳን ወደ ስደት ሲጀምሩ ወደ አሜሪካን ሀገር ሂደው ለመማር ጉጉት የነበራቸው ፠ሱዳን ገደሀሪፍ ከተማ አንድ የማይደራደሩት ፈተና ገጠማቸው።ኢህዴን የሚባል ድርጅት የአማራውን ህዝብና ሌላውን ብሄረሰብ ኦሮሞውን ደቡቡንም በኢትዬጵያዊነት ስም እያታገለ ለደርግ ውድቀት ከፍተኛ ሚና የተጫወተ ድርጅት ነው ። ከደርግ ውድቀት በሆላ ግን የህወሀትን ሴራ የሚያውቁ ለአማራ ህዝብ ለመታገል የሞከሩት ታጋይ ሙሉአለም አበበ የኢህዴን መስራች ና የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባልና የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበረ ።ዘሩ ቤተስራኤል የሚመዘዝ መላው ቤተሰቡ ወላጆቹ እስራኤል ሀገር የሚኖሩ እስራኤል ሀገር መኖር እየቻለ የታገልሁለት የአማራ ህዝብ ሙሉ ተጠቃሚ ሳይሆ…ን ኢትዬጵያን ትቸ አልሄድም በማለቱ የታገለለት ህዝብም ከመከራ ከጭቆና ከሞት ሳይላቀቅ ኖረ። ታጋይ ሙሉአለም አበበ ህልሙን ጉዞውን ሳይጨርስ በፀረ አማራዎች በታደሰ ካሳና በበረከት ስምዖን ገዳይ ቡድን ደብረ ማርቆስ ቤተመንግስት በፈንጅ ህይወታቸው እንዲያልፍ ሁኖል። ከአንዳርጌ አበበ ቢሮ ተገድሎ ተገኘ ተብሎ በበረከት ስምዖን አንዳርጌ ገዳይ ተብሎ በግምገማ ተወነጀለ። አላማው አማራዎችን እያሳደዱ መግደልና ማሰር ነበር ። ፈተናውም ለኢትዬጵያ ህዝብ ነፃነት የሚታገል ኢህዴን የሚባል ድርጅት እንዳለ በአቶ አዲሱ ለገሰ ተነገራቸው፠በቀናህነት ለህዝብ በማሰብ ተሰድጀ ውጭሀገር በድሎት ከመኖር ለምን ወገኔን ነፃ ቢወጣ ለህዝብ መታገልን መርጠው ትግሉን ቀጠሉ፠በረሀ ወታደራዊ ስልጠና (ታሊም) እየሰለጠኑ እያለ በነበራቸው አመለካከትና የተሻለ ፖለቲካውንም በጥልቀት አንብበው መረዳት የሚችሉ ስለነበር የተለየ ተልእኮ በተሰጣቸው ሰዎች ማሰልጠኛ በጥይት ተመትተው ቆስለው ከሞት ተርፈዎል፠ስልጠናቸውን እንደጨረሱ ትግራይ በረሀ በሚተላለፍ ሬድዬ ፕሮግራም ላይ ሁለት የህወሀት ታጋዬችና ከኢህዴን የኢህዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ከነበረው መዝሙር ፈንቴ ጋር ልክ ዜና አዘጋጅ የፕሮፖጋንዳ ስራ በማቀነባበር ለትግሉ ትልቅ ሚና ነበራቸው፠ በ1983 የደረግ ስርአት ሲለወጥ ባህርዳር የክፍለሀገር ኮሚቴ በመሆን የሰሩ ነበሩ ከነዚህም ዝርዝር፠ 1ኛ አንዳርጌ አበበ የሞጣ ተወላጅ ገዳም ይገኛሉ 2ኛ ሸጋው ጥሩነህ የመርጦ ለማሪያም ተወላጅ ሁለት እጁ እነሴ ሽፍታ ገደላቸው በሚል ህይወታቸው እንዲያልፍ ሁነዎል፠ 3ኛ ታደሰ ካሳ ትግራይ ተወላጅ የአማራ ክልል ፈላጭ ቆራጭ በመሆን እስርቤት እስከገባበት ድረስ ቆይቷል፠ 5ኛ ገብረእግዚአብሄር የትግራይ ተወላጅ ጋር አብረው በኮሚቴ በመሆን ሰርተዎል፠ ታጋይ አንዳርጌ አበበ የአማራ ክልል ምክርቤት በ1984 ሰኔወር ሲቋቋም መድረኩን ይመሩ ነበር በወቅቱ በፖለቲካ ውሳኔ አዲሱ ለገሰ ፕሬዝዳንት፡ አያሌው ጎበዜ ም/ፕሬዝዳንት፡ ንብረቱ ገነቱ ፅሀፊ አድርጎ የክልሉ ስራአስፈፃሚ ድልድሉን መድረኩን በበላይነት ይመሩት ነበር። በዚያን ወቅት ደመቀ መኮነን የሚባል የአማራ ነፃ አውጭ አይታወቅም ነበር። ከተወሰኑ አመታት በሆላ የክልሉ ምክር ቤት ፅሀፊ ለአማራ ህዝብ የሚቆረቆር ጠንከር ያለ አቋም ስለነበረው በነታደሰ ካሳ ከምክርቤቱ እንዲባረሩ ሁኖል። የክልል ምክርቤት አባል ህዝብ የወከላቸው ከህዝብ እውቅና ውጭ በወቅቱ ባችለር ዲግሪ የነበራቸው በ6ኛ ክፍል ተማሪ በታደሰ ካሳ አጋፍሪነት እንዲባረሩ ተደርጎል። በአቶ ንብረቱ ገነቱ ምትክ አቶ ደመቀ መኮነን የክልሉ ምክርቤት ፅሀፊ ሁነው ተሾሙ። አቶ ባንታምላክ አላምነው የአማራ ክልል ምክርቤት ስራአስፈፃሚ የግብርና ዘርፍ ሀላፊ የነበሩ በታደሰ ካሳና መሰል ፀረ አማራዎች የኢሠፓ አባል ያልሆኑትን ከእነሱ እውቀት በላይ ስለሆኑ የኢሠፖ አባል ሳይሆኑ በሠሩበት ዳንግላ የፖርቲ አባል ሊስት ላይም አልተገኘም በዚያን ወቅት የአገውምድር አውራጃ ኢሠፖ አመራር የነበሩት ባለስልጣኖች ለማጣራት ተሞክሮ ምንም የተገኘ ማስረጃ ሳይገኝ በታደሰ ካሳ የተሰጣቸው ወንጀል ሙህራዊ ትምክህት ይሆናል። በዚያን ወቅት ከ6ኛ ክፍል ያልደረሱ ከፍተኛ አመራሮች ከ8ኛ ክፍል በላይ የሆኑ አመራሮች ሙህር ተብለው ስለሚመደቡ ተጠንቅቀህ ስብሰባ ላይ ካልተናገርህ የተማርኸው ዶክትሬት በ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተገመገምህ አብደህ ትለቃለህ አለያ አስተሳሰብህ ከ6ኛ ክፍል ተማሪው ያነሰ አስተሳሰብ ከያዝህ በስልጣን ትቀጥላለህ ። ተሳስተህ አንድ የእንግሊዘኛ ቃላት ከአፍህ ከወጣች በሙህራዊ ትምክህት አንድ ሙሉቀን ሙሉ ትገመገማለህ። የቀድሞ ሰራዊት ኦፊሰር የነበሩ አቶ እንዳወቀ ገላው የአዊ ዞን አስተዳዳሪ የነበሩና ዞኑ ሲመሰረት የመጀመሪያው አስተዳዳሪ የነበሩ። ዞኑ እንጅባራ እንዲሆን የሳቸው አስተዎፅኦ እጅግ ከፍተኛ ነው ተብለው በአንዳንዶች የሚታሙ።የአገው ህዝብ በነበረከትና በታደሰ ካሳየአማራን ና አገውን የመከፍፈል ፕሮጀክት ያልተቀበለ ። የአገው ህዝብ በኢትዬጵዪዊነቱ ቅንጣት ያህል እንዳይደራደር ያደረገ ቁርጠኛ መሪ የነበረና የብአዴን ወታደሮችን አሰልጣኝ የነበረ ። በነ ታደሰ ካሳ ጠንካራ ኢትዬጵያዊነቱ ስላልተወደደ ከአመራርነት በፀረ አማራዎች እንዲነሳ ሁኖል። አዊ ዞን ሲዎቀር ጠንካራ መሰረት እንዲይዝ የዞኑ መምሪያዎች በአካባቢው ተወላጅ የተማሩ ሰዎች መመደብና የሚመራቸው ወረዳወችና የዞን መምሪያዎች ያለ ጣልቃገብነት የመራ በሳል አመራር ነበር። በተለይ በሽግግሩ ዘመን ማንም ካድሬ እንደፈለገ በሚታሰርበት ወቅት ይከላከሉ ነበር። የቀድሞ መንግስት የጦር መኮነን ስለነበሩ በብአዴን ካድሬዎች አልተወደዱም። ለእንደዚህ ያሉ የሀገር ባለውለታዎች የክልሉ መንግስት እውቅና ሊሰጣቸው ይገባል። ከ1984 ሰኔ ወር ጀምሮ አንዳርጌ ሞጣን በመወከል የክልል ምክርቤት አባል በመሆን የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳዳሪ በመሆን ተመድበ ሀገርን በቀናህነት ያገለገሉ ግለሰብ ። በበረከት ስምዖንና በታደሰ ካሳ ጥርስ ውስጥ ስለገቡ በፕላን የአማራ ተወላጆች የሌላ አካባቢውን በደምብ ባላውቀውም በአንዳርጌ አበበ ላይ የደረሰው ግፍ ግን ሞራላቸውን ለመንካት ያልተፈፀመባቸው ግፍ የለም፠ በ1985 ታጋይ ሙሉአለም አበበ የበአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ና የኢህዴን መስራች ና የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበረ በዘህዉ አመት ወሎ መድረክ እነ በረከትንና ከፍተኛ አመራሮችን በመገምገማቸው ወደ አማራ ክልል ኢህዴን ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሁነው እንዲመደቡ ሁነው፠ የወሎውን የታጋዬችን የመደረክ ውሎ ላልተሳተፉ ታጋዬች እንዲያወያዩ ታጋይ ሙሉአለም አበበ ደብረማርቆስ ለማስገምገም ሄዱ ግምገማውን ሲያስገመግሙ ሰንብተው ፠በአንድ በተረገመ ምሽት የታጋይ ሙሉአለም አበበ ሹፌርና አጃቢዎች በክልሉ የአስተዳደርና ፀጥታ ሀላፊ በአቶ ታደሰ ካሳ እንደተጠሩ ነው የሚነገረው፠ ያለጠባቂ እንዲቀር ሁኖ ሞች ሙሉአለም ይወቅ አይወቅ ባልታወቀበት ምክንያት ለህልፈት በቅተዎል፠ በጣም የሚያሳዝነው ግን ሙሉአለም አበበ ከአንዳርጌ አበበ ቢሮ በፈንጅ እንዲገደሉ ተደረገው፠ በረከት ስምዖን ሙሉአለም አበበን ማንገደለው ብሎ በግምገማው ወቅት እጁን ወደ አንዳርጌ አበበ አዞረ ፠ መሉአለም ሲገደል ፈንጅ ሲፈነዳ እንዴት አልሰማህም ብሎ የምስራቅ ጎጃም የተመደበ ካድሬ በአጠቃላይ በበረከት መሪነት ንፁሁን መናኙን ታጋይ አንዳርጌ አበበ ላይ ተረባረቡበት ፠ አንዳርጌ አበበ ለሙሉአለም አበበ ቢሮቸውን ሰጥተው በስልክ ለበረከት ሪፖርት እያቀረበ እያለ እንደተገደለ በረከት አድርባይ ካድሬዎችን በራሳው የማይተማመኑትን ና ስልጣን ፈላጊዎች ለአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ የሆነውን አንዳርጌ አበበ በ1985 ከድርጅትም ሆነ ከመንግስት ስልጣን መቀጠል አልፈልግም ንፁህ ሰው ወንጅላችሁ ወደ ዞን አስተዳሪነትም ከድርጅቱም መቀጠል እንደማይፈልጉ ለአቶ አዱሱ ለገሰ ገልፀውላቸው ድርጅቱን ተሰናበቱ፠ አንዳርጌ አበበ በግምገማው ላይ በበረከት መወንጀል ያልዳኑ አንዳርጌ አበበ መድረክ ላይ በግልፅ መግደል ቢገባኝ እንኳን ፀረ አማራውን አንተን ነበር በማለት በረከት ስምዖንን የአማራውን ቅኝ ገዥ በረሀ ጀምረው በፀረ አማራነት ስለሚያውቁት ተባባሪ ባያገኙም በረከትና ታደሰን በድፍረት ከበረሀ ጀምሮ በመታገላቸው የበረከት ሰለባ እንዲሆኑ ሁኖል። መናኙ ታጋይ አባ አንዳርጌ አበበ በግልፅ መድረክ ላይ ኢህዴን ብአዴን የህዝብ ትመስለኝ ነበር የበረከት የግል ድርጅቱ መሆኑን በጊዜ ያጋለጡ ያልተዘመረላቸው ባለታሪክ ጀግና ገዳም ይገኛሉ። በረከት በሙሉአለም አበበ ግድያ በግምገማ ከካድሬዎች ፊት ሲወነጅላቸው መናኙ አንዳርጌ አበበ የተገደለው ቀላል ሰው አደለም የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ሙሉአለም አበበ ነው የተገደለው በረከት አታድበስብሰው መረጃ እያጠፍህ ነው ፖሊስ ምርመራውን በህጋዊ መንገድ ያጣራው እያሉ ቢናገሩ ሰሚ አልነበረም። የአማራ ህዝብ አዳኝም ገዳይም በረከት ስስምዖን ስለነበረ። ታጋይ አንዳርጌ አበበ በእጀ የሰው ህይወት አጥፍቸ አላውቅም ንዴት በተሞላው ንግግር መግደል ቢገባ እንኳን ፀረ አማራው በረከት አንተን ነበር የምገድለው በማለት በንዴት ይናገራሉ።ታጋይ ሙሉአለም አበበን ለአማራህዝብ ተቆርቋ ወንድሜን መካሪየን ጎዴን እንዴት እገድላለሁ ብለው ከተሰብሳቢው ፊት በድፍረት ተናግረዎል። በወቅቱ የነበሩ የብአዴን አመራሮች የበረከት ስምዖንና የታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ጉዳይ አስፈፃሚ የማደጎ ልጆቹ ስለሆኑ ቃልኪዳናቸውን ጠብቀው ፍትህ ሳያገኙ የለውጡ ሀይልም የተፈፀመውን ወንጀል በችልተኝነት ማየቱ እጅግ አሳዝኖኛል።ደብረማርቆስ ከ50 በላይ የተሰበሰበው የብአዴን ካድሬ የበረከት ቃልን በማክበር አንዳርጌ ተሰናበ። በወቅቱ የምስራቅ ጎጃም ዞን ኢህዴን ፅሀፊ የነበሩት ታጋይ ስማቸው ጎበዜ ስብሰባው ላይ የሙሉአለም አበበ ሹፌርና አጃቢዎችን ማን ወደ ክልል ጠራቸው ብሎ ሲጠይቅ። በረከት ለስማቸው የመለሰለት መልስ ውስጣችሁን እዩ ችግሩን ወደ አንዳርጌ አበበ ተደረገ። ስማቸው ጎበዜ ከዞኑ ኢህዴን ፅሀፊነት ታገደ ። በበረከት ስምኦንና በታደ ካሳ የአማራ አመራሮች ህይወታቸው እንዲመሰቃቀል ትዳራቸው እንዲፈርስ ሁኖል። በተሰናበቱ ከአንድ አመት በሆላ በአማራ ክልል የፀጥታ ፕላን በ1986 እንደማንኛውም የአማራ ህዝብ በደረቅ ጣቢያ ባህርዳር ከ2 አመት በላይ ታስረዎል በሙሉአለም ክስ ነፃ ተብለው ሲፈቱ እንደገና በደርግ ቀይሽብር ተዎናይ ነበሩ ተብለው በሀሰት ምስክር እንዲፈረድባቸው ሁኖል፠ በድምሩ ወደ 9 አመት ታሰሩ ፠ ሲፈቱ ዳግም ወደ እስር ላለመወርወርና ህይወታቸውን ለማቆየት ላይመለሱ በእግዚአብሄር ቤት ፀንተው በምነና አለምን ንቀው ገዳም ይገኛሉ፠ እኒህ ግለሰብ ለኢትዬጵያ ፖለቲከኞች ስልጣን ምንም እንዳልሆነ ያሳዩ የአማራ ብርቅየ ልጅ ናቸው ።ታሪካቸው ቢፃፍ ቢዘገብ ለአማራ አንድነት ለኢትዬጽያ አንድነት ጠቀሜታ አለው ብየ አስባለሁ፠ የአማራ ብልፅግና አመራሮች ከአቶ አገኘሁ ተሻገር ጀምሮ የአማራ ማስሚዲያ ከፍተኛ አመራሮች የአንዳርጌ አበበ ያሳለፉት መከራ ትውልድ እንዳይማርበት በሚዲያ እንዲዘገብ አልተፈለገም። ሌላው ታጋይ ሸጋው ጥሩነህ ሞጣ ሆስፒታል በስሙ እንዲሰየም የተደረገለት የመርጦለማሪያም ተወላጅ ታደሰ ካሳ ጋር የሪጅን ኮሚቴ ሁኖ እየሰራ ሁለት እጁ እነሴ የፀጥታ ችግር አለ አረጋጋ ተብሎ በሽፍታ ተገደለ በሚል በተቀነባበረ መንገድ እንዲገደል ሁኖል። በነታደሰ ካሳ ግዳጅ እንደ አንድ የወረዳካድሬ ግዳጅ ተሰጥቶት ሲሄድ ለታጋይ አንዳርጌ አበበ እነበረከትና ታደሰ ያሴሩበት ሴራ ታይቶት አንዳርጌ አበበን ደህና ሁን ከእንግዲህ በህይወት አንገናኝም ብሎ ተሰናብቶት ህይወቱ ተቀጥፎ ቀረ የአማራን ህዝብ እኛ ካልታደግነው ህወሀቶች የአማራን ህዝብ እንዳይጨርሱት ህዝቡን ለመታደግ ሙሉ እምነት የነበራቸው በነበረከት ና ታደሰ እንዲጠፉ ሁነዎል።በረከት ስምዖን ና ታደ ሰ ካሳን የፈፀሙት ወንጀል እንዳይጋለጥ የቆመላቸው በለውጥ ሀይል ስም በአማራ ክልል አመራሮች የነበረከት ወኪሎችን ከሀላፊነት ማንሳት የርእሰ መስተዳድሩ ዶክተር ይልቃል ከፍለና የም/ርዕሰ መስተዳድሩ የዶክተር ጌታነህ ጀምበር ትልቅ የቤት ስራ ይጠበቅባቸዎል። ከቀድሞ የኢህዴን ብአዴን የጎጃም አገው አማራ ታጋይ የተከተበ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply