You are currently viewing አብንን ማን እየጋለበው ነው?!   ባህርዳር ። ግንቦት 01/2014/ዓ.ም             አሻራ ሚዲያ አብን ለአቶ ክርስቲያን ታደለ ማስጠንቀቂያ ሰጥቻለሁ ብ…

አብንን ማን እየጋለበው ነው?! ባህርዳር ። ግንቦት 01/2014/ዓ.ም አሻራ ሚዲያ አብን ለአቶ ክርስቲያን ታደለ ማስጠንቀቂያ ሰጥቻለሁ ብ…

አብንን ማን እየጋለበው ነው?! ባህርዳር ። ግንቦት 01/2014/ዓ.ም አሻራ ሚዲያ አብን ለአቶ ክርስቲያን ታደለ ማስጠንቀቂያ ሰጥቻለሁ ብሏል። ለአቶ ክርስቲያን ማስጠንቀቂያ የሰጠሁት አንጃ በመፍጠር፣ የአብን መርህ ባለማክበር እና ህግ በመጣስ ነው ብሏል። አቶ ክርስቲያ በበኩላቸው ራሳቸው ባልተሳተፉበት ስራ አስፈፃሚ እንደዚህ አይነት መወሰኑ ህጋዊ እንዳልሆነ ገልፀዋል። ንቅናቄው ለቀጣይ ስራ እንዲታገልም ጥሪ አስተላልፈዋል። አብን ሌሎች የንቅናቄው አባላትም ማስጠንቀቂያ እና ማገጃ ጥሏል። አብን ያገደው በባለፈው መጋቢት 11 ቀን 2014 ዓም በተደረገው ጉባዔ ላይ ተቃውሞ ያነሱት መሆኑ ልዮ ግርምትን ፈጥሯል። በባለፈው መጋቢት 11 ቀን 2014 ዓም በባህርዳር ሙሉዓለም የባህል አዳራሽ በተደረገ ጉባዔ 580 አባላት ተሳትፈዋል። ነገርግን ይሄን ጉባዔ ምርጫ ቦርድ ሳያፀድቀው ቀርቷል። ምርጫ ቦርድ የአብን ጉባዔ ያላፀደቀው በሶስት መሰረታዊ ምክንያቶች ነው። የመጀመሪያው፣ የአብን የምክርቤት አባላት በስራ አስፈፃሚው ሀሳብ ባለመስማማታቸው ነው። ስራ አስፈፃሚው ለብልፅግና የተመቹ ስራ አስፈፃሚዎችን ይዞ በመቅረብ ጉባዔተኛውን አፅድቁልኝ አለ። ጉባዔተኛው ግን በአብን ስራ አስፈፃሚ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ያስፈልጋል በሚለው አቋሙ ፀና። ጉባኤተኛው የአብን ስራ አስፈፃሚ ለአብን ሳያሳውቅ ከብልፅግና ስልጣን ያላግባብ መቀበሉ በአባሉ ዘንድ ከፍ ያለ ቅሬታ አስቀርቧል። የአብን ስራ አስፈፃሚዎች ከብልፅግና ስልጣን የተጋሩት ፣ በአብን ፈቃድ እና ስምምነት ሳይሆን በብልፅግና ፈቃድ ነው። አብን የብልፅግና ገባሪ ሆኖ ነው። በዚህ ምክንያት የአብን ጉባዔተኛ ፣ ሳይስማማ እስከ ሌሊቱ አምስት ሰዓት ተወያዮ። እነ በለጠ ሞላ ግን ስብሰባ ረግጠው ወጡ። ይህም ከአብን አባላት በተጨማሪ ምርጫ ቦርድን አሳዝኗል። ሌላኛው የአብን ጉባዔ ሳይፀድቅ የቀረበት ምክንያት የአብን ስራ አስፈፃሚ አባላት በተለይ እነ በለጠ ሞላ የምርጫ ቦርድ ታዛቢዎችን ለታዛቢነት ቀረፃ እንዳያደርጉ በማገዳቸው ነው። የአብንን ጉባዔ የምርጫ ቦርድ አልቀረፀውም። አብን አምባገነን ሆኗል። ይህም መሰረታዊ የፓርቲዎችን እና የምርጫ ቦርድን ህጋዊ ግንኙነት የጣሰ ነበር። ሶስተኛው የአብን ጉባዔ የተሰረዘበት ዋነኛ ምክንያት የመተዳደሪያ ደንቡ መሰረታዊ የግልፅነት፣ የህግ፣ የአመክንዮ ስህተት ስለተገኘበት ነው። በእነዚህ ሶስት መሰረታዊ ስህተቶች ምክንያት የአብን ጉባዔ ተሰርዟል። አብን እስከ ሰኔ 18 ቀን 2014 ዓም ጉባዔ አድርጎ ማሻሻያ ካላደረገ የፓርቲው ህልውና ሙሉ በሙሉ ይከስማል።ይሄን የሰጋው የአብን ስራ አስፈፃሚ ቡድን ህዝባዊ ተቀባይነት ያላቸውን መሪዎች፣ የአብን ግድፈት ለማረም የሚንቀሳቀሱ አባላትን በማገደድ እና በማስጠንቀቅ መግለጫ አውጥቷል። ማገድ የሚችለው ማዕከላዊ ኮሚቴው እና ጉባዔተኛው ቢሆን ህጋዊነት የጎደላቸው ውስን የአብን ስራ አስፈፃሚዎች ለስልጣን በመሳሳት የሚቃወሟቸውን አግደዋል። አብን በብልፅግና መንገድ እየተጓዘ አድርባይነትን ተላብሷል። ለስልጣን ብሎ መከፋፈልን ተለማምዷል። ህወሃት ለወረራ እየተዘጋጀ፣ አማራ በአራቱም አቅጣጫ ተወጥሮ እያለ አብን የተባለው ፓርቲ በስልጣን ሲጣላ፣ በክህደት ቁልቁለት ወድቆ ለብልፅግና ጌቶች ሎሌ ሆኗል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply