አብን በተለያዩ አካባቢዎች የሚያደርገውን የምርጫ ቅስቀሳ አጠናክሮ በመቀጠል በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ላሎ ወረዳ ወገሬ ከተማ፣ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በተለያዩ

አብን በተለያዩ አካባቢዎች የሚያደርገውን የምርጫ ቅስቀሳ አጠናክሮ በመቀጠል በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ላሎ ወረዳ ወገሬ ከተማ፣ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች፣ በሚዳ ወረሞ ወረዳ በኮሶ ማርያም፣ በግርግር፣ በተጎራ ማርያምና በደንጎሬ ቀበሌዎች ቅስቀሳ ማድረጉን አስታውቋል።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ሚያዝያ 5 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ

ሕዝቡ የምርጫ ካርዱን በማውጣት እና ኃቀኛ ወኪሉን በመምረጥ ነገውን የተሻለ እንዲያደርግ የጠየቀው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ቀጣዩን ምርጫ አሸንፎ መዋቅራዊና ሥርዓታዊ ችግሮችን በማስወገድ አገርና ሕዝብን የሚታደጉ የበጎ ኃይሎች ጥምረት መሰባሰቢያ እንዲሆን አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን ገልጧል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ላሎ ወረዳ ወገሬ ከተማ፣ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች፣ በሚዳ ወረሞ ወረዳ በኮሶ ማርያም፣ በግርግር፣ በተጎራ ማርያምና በደንጎሬ ቀበሌዎች የተሳኩ የምረጡኝ ቅስቀሳዎችን ማካሄዱን ያስታወቀው አብን
የምርጫ ካርድ በማውጣት ዴሞክራሲያዊ መብቱን በመጠቀም ሥርዓትና መዋቅር ሰራሽ ችግሮችንእንዲያስወግድ ጥሪ አድርጓል።

በምርጫ ቅስቀሳ መረኃ ግብሮቹ ላይ በአቶ በሪሁን አስፈራው ላይ የተፈጸመውን ግድያ ያወገዙ ሲሆን በኦሮሚያ፣ በቤንሻንጉል፣ በአጣዬና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመው ጅምላ ጭፍጨፋ እንዲያበቃ መንግስት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ተጠይቋል።

“አማራ በኃቀኛ ልጆቹ የሚወከልበት ጊዜው አሁን ነው፤ ነፃ ያወጣናቸው የትላንት ጨቋኞቻችንን የአፈና አካሄድ በካርዳችን አባረን የሁሉም የሆነ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንገነባለን፤ እኛም በሪሁን አስፈራው ነን” ብለዋል ተሳታፊዎቹ።

በተጨማሪም “ለሕዝባችን ነፃነት ሰማእት የሆኑ ወገኖቻችንን ሰማእትነት የሚመጥን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት አብን ምርጫችን ነው፤ ካርዳችን ለነፃነታችን ደጀን ለአብን እንሰጣለን!” የሚሉ መልዕክቶችም ተላልፈዋል ያለው አብን “የመዋቅርና ሕግ ሰራሽ ችግሮችን ሰንኮፍ ነቅሎ ዲሞክራሲን ማስፈኛ ጊዜው አሁን ነው!” መሆኑን ጠቁሟል።


Source:- አማራ ሚዲያ ማዕከል

Source: Link to the Post

Leave a Reply