አብን የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደግፍ የአማራ ወጣቶች ማህበር አስታወቀ።   አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህ…

አብን የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደግፍ የአማራ ወጣቶች ማህበር አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህ…

አብን የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደግፍ የአማራ ወጣቶች ማህበር አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር ለሚዲያችን እንዳስታወቀው አብን በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀልን ለማውገዝ የፊታችን ረቡዕ እና እሁድ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ለሰብዓዊነት የተጠራ በመሆኑ ሁሉም ሊደግፋው የሚገባ ነው ብሏል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ሳይቀር ይህን ለሰብዓዊነት ክብር ሲባል የተጠራ ሰልፍ እንዲደግፉት ሲልም ጥሪ አቅርቧል። የማህበሩ ሰብሳቢ ወጣት አስናቀ መንገሻ እንደገለጸው ሰልፉን መንግስት ጣልቃ ገብቶ የሚያስተጓጉል ከሆነ ማህበራችን ከሰላማዊ ትግሉ በመውጣት ሌሎች አማራጮችን ለመውሰድ ይገደዳል ብሏል። ስለሆነም መንግስት በሰልፉ የሚነሱ ጥያቄዎችን በአግባቡ መፍታት እንዳለበት ነው ያሳሰበው። ሰልፉን አብን ቢጠራውም ጉዳዩ የሁላችንም በመሆኑ በየከተማው ያሉ ሰልፎችን ማህበሩ በማስተባበር ሀላፊነቱን እንደሚወጣም ወጣት አስናቀ ገልጿል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply