አተማ  በአማራ ሀኪሞች ላይ የሚደርስውን በደል  አጥብቆ ያወግዛል ሲል አሳሰበ። (አሻራ፣ሚዲያ መጋቢት 7/2013 ዓ•ም ባሕርዳር) በዛሬው እለት ማለትም በቀን 06/07/2013 ዓ/ም  በባህ…

አተማ በአማራ ሀኪሞች ላይ የሚደርስውን በደል አጥብቆ ያወግዛል ሲል አሳሰበ። (አሻራ፣ሚዲያ መጋቢት 7/2013 ዓ•ም ባሕርዳር) በዛሬው እለት ማለትም በቀን 06/07/2013 ዓ/ም በባህ…

አተማ በአማራ ሀኪሞች ላይ የሚደርስውን በደል አጥብቆ ያወግዛል ሲል አሳሰበ። (አሻራ፣ሚዲያ መጋቢት 7/2013 ዓ•ም ባሕርዳር) በዛሬው እለት ማለትም በቀን 06/07/2013 ዓ/ም በባህርዳር ከተማ ለተቃውሞ የወጡት በብርታት ተምረው የተመሠቁ ብቁ የህክምና ባለሙያዎች ናቸው። አንዳንዶቻቸውም በተማሪነታቸው አባላቶቻችን የነበሩ እና ለተቋማችን የጀርባ አጥንት የነበሩ፤ በተሰለፉበት ሁሉ የማያሳፍሩ ታታሪ ጠቅላላ ሀኪሞች ናቸው። ይሁንና ከ10 የኢትዮጵያ ክልሎች በተለየ ሁኔታ የአማራ ሀኪሞች እንዳይቀጠሩ ተደርጓል። ይህ የአማራን ምሁር የማሳደድ አባዜ አተማን በ2 ምክንያት ያሳስበዋል። 1.ይህ የክልሉ መንግስትና የክልሉ ጤና ቢሮ እየሰራ ያለው ሥህተት አተማ ለቆመለት የትምህርት ጥራት እንቅፋት ነው። ጎበዝ ተማሪዎችን ከጨዋታ ሜዳ ውጭ የማድርግ ስርዓት የትምህርት ጥራቱን ክፉኛ ጎታችና ስልጡን አዕምሮን መጨፍለቅም ነው። 2.ሩቅ ኪሎሜትር አቋርጠው፤ ንብረታቸውን ሽጠው ለህክምና የሚመጡ ሚሊዮን የአማራ ገበሬዎች በህክምና እጦት በሚሰቃዩበት ክልል 400 ስራ አጥ ሀኪም ማየት አደገኛ እውነት ነው። በእናቶች ሞት መሪ የሆነ ክልል ሀኪም አለመፈለጉም ግሩም ነው። በመሆኑም የአማራ ክልል መንግስት የአማራ ሀኪሞችን መቅጠር ብቻ ሳይሆን ለሀኪሞች ምቹ ክልል በመፍጠር ታላቁ የአማራ ህዝብ ፈጣንና ጥራት ያለው ህክምና እንዲያገኝ ማድርግ ይኖርበታል። በሌላ በኩል አማራን ለይቶ የማሳደድ፣ የመግደልና የማድህየት ሁኔታ የኦሮሞ መራሹ የፌደራል መንግስት አላማና ግብ እየሆነ መምጣቱን ታዝበናል። የአማራ ሀኪሞች እንቅሰቃሴም ከዚሁ አኳያ እንዲቃኝ አተማ መልዕክቱን ያስተላልፋል። አማራነት በከዋክብት ልጆቹ ይደምቃል!! አተማ መጋቢት 6/2013 ዓ.ም https://youtu.be/TKrRqv74f2k

Source: Link to the Post

Leave a Reply