አቶ ልደቱ አያሌው በተከሰሱበት ህገ-ወጥ መሣሪያ ይዞ መገኘት ክስ ለታህሳስ 7 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ህዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸ…

አቶ ልደቱ አያሌው በተከሰሱበት ህገ-ወጥ መሣሪያ ይዞ መገኘት ክስ ለታህሳስ 7 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸ…

አቶ ልደቱ አያሌው በተከሰሱበት ህገ-ወጥ መሣሪያ ይዞ መገኘት ክስ ለታህሳስ 7 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አቶ ልደቱ አያሌው ዛሬ ህዳር 16 ቀን 2013 ዓ/ም ከጠዋቱ በ4 ሰዓት አዳማ በሚገኘው ምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ከዚህ ቀደም በነበረው ችሎት በተከሰሱበት ህገ-ወጥ መሣሪያ ይዞ መገኘት ክስ የመከላከያ ምስክር አቶ ልደቱ እንዲያቀርቡ ችሎቱ ማዘዙ ይታወሳል። በዛሬው ችሎትም አቶ ልደቱ ከጠበቆቻቸው ጠበቃ አብዱልጀባር ሁሴን እና ጠበቃ ገመቹ ጋር ቀርበዋል። የአቶ ልደቱ ጠበቆችም በዛሬው ችሎት በታዘዝነው መሠረት መከላከያ ምስክሮቻችንን ማቅረብ አልቻልንም፤ ምክንያቱም ባለፉት ሳምንታት አቶ ልደቱ ከልብ ህመማቸው ጋር ተያይዞ የህክምና ክትትል ላይ ስለነበሩ በቂ ምክክር አላደረግንም ስለዚህ ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠን ብለው ጠይቀዋል። ለችሎቱም አቶ ልደቱ 6 የመከላከያ ምስክሮችን እንደሚያቀርቡ የተገለፀ ሲሆን በዚህ መሠረት ተለዋጭ ቀጠሮ ለታህሳስ 7 ቀን 2013 ዓ/ም ከጠዋቱ በ4 ሰዓት እንዲቀርቡ መሰጠቱን የኢዴፓ ፕሬዚዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ለብስራት ተናግረዋል። ብስራት ራዲዮ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply