አቶ ልደቱ አያሌው ናዝሬት/ አዳማ በሚገኘው ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ቋሚ ምድብ ችሎት ቀርበው ለህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል…

አቶ ልደቱ አያሌው ናዝሬት/ አዳማ በሚገኘው ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ቋሚ ምድብ ችሎት ቀርበው ለህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል…

አቶ ልደቱ አያሌው ናዝሬት/ አዳማ በሚገኘው ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ቋሚ ምድብ ችሎት ቀርበው ለህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 20 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የዛሬው የአቶ ልደቱ ቀጠሮ “ሕገመንግስቱን በኃይል ለመናድ፤ የሽግግር መንግስት ሰነድ በማዘጋጀት፤ ከድጡ ወደ ማጡ የተሰኘ ለውጡን የሚቃወም መጽሃፍ በመጻፍ፤ …” በሚል የኦሮሚያ ክልል መንግስት ዓቃቤ ሕግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ ጠበቆቻቸው ያቀረቡትን የመጀመሪያ የክስ መቃወሚያ ላይ ብይን መስጠት (ያስከስሳል ወይስ አያስከስስም በሚለው ላይ) እንዲሁም የቀረበውን የዋስትና መብት መርምሮ ለመፍቀድ ነበር። በዚህ መሰረት ዐቃቤ ህግ፣ አቶ ልደቱ እና የአቶ ልደቱ ጠበቆች 8.40 ላይ በተሰየመው ችሎት ቀርበዋል። ችሎቱ “የመጀመሪያ መቃወሚያ የቃል ክርክሩ ወደ ፅሁፍ ተገልብጦ ስላልደረሰ በዛሬ ችሎት ጉዳዩን መርምረን ብይን ለመስጠት አልቻልንም፤ ስለዚህ ተለዋጭ ቀጠሮ ለመስጠት እንገደዳለን በዚህ ላይ አቃቢ ህግ እና ጠበቆች አስተያየት ካላችሁ ” ሲል ገልጿል። አቃቢ ህግ ተቃውሞ እንደሌለው ሲያስታውቅ የአቶ ልደቱ ጠበቆች ግን የተፋጠነ ፍትህ እንደሚያስፈልግ፤ አቶ ልደቱ እያመማቸው እንደሆነ፤ በ48 ሰአት ውስጥ የዋስትና ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ ህጉ ቢደነግግም ጥያቄ ካቀረቡ ሳምንት እንዳለፈ በማመልከት ችሎቱ የቃል ክርክሩን መሠረት አድርጎ በዋስትናው ላይ ብይን ሊሰጠን ይገባል በማለት አቤቱታ አቅርበዋል። ችሎቱም አቶ ልደቱ የተፋጠነ ፍትህ ማግኘት እንዳለባቸው እንደሚያምን፤ ነገር ግን የቃል ክርክሩ በፅሁፍ ተገልብጦ መመርመር ሳይችል ዋስትና መፍቀድ አንደማይችል ገለጿል። ከሚቀጥለው ቀጠሮ በፊት የቃል ተቃውሞው በጽሁፍ ተገልብጦ ከደረሰ ችሎቱ ሊያየው እንደሚችል በመግለጽ የዋስትና ጥያቄው ላይም ሆነ የመጀመርያ ደረጃ መቃወሚያው ላይ ብይን ለመስጠት ለህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4 ሰአት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን በስፍራው የተገኙት የኢዴፓ ፕሬዚደንት ገልጸውልናል ሲል ኢዴፓ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply