አቶ ልደቱ አያሌው ከተመሠረተባቸው “ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት” የሚል ክስ ፍርድ ቤት ነጻ ናቸው ብሎ እንደፈረደላቸው ተሰማ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥር 12 ቀን 201…

አቶ ልደቱ አያሌው ከተመሠረተባቸው “ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት” የሚል ክስ ፍርድ ቤት ነጻ ናቸው ብሎ እንደፈረደላቸው ተሰማ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 12 ቀን 201…

አቶ ልደቱ አያሌው ከተመሠረተባቸው “ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት” የሚል ክስ ፍርድ ቤት ነጻ ናቸው ብሎ እንደፈረደላቸው ተሰማ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የድምጻዊ ሐጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በቢሾፍቱ በተቀሰቀሰ ሁከት ላይ ሁከቱን አስተባብረዋል፣ በገንዘብም ረድተዋል በሚል በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው፣ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ከቀረበባቸው “ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት” የሚል ክስ ፍርድ ቤት ነጻ ናቸው ብሎ እንደፈረደላቸው ተሰማ፡፡ ዛሬ ዕለተ ረቡዕ ጥር 12፣2013 በነበራቸው የፍርድ ቤት ቀጠሮ የውሳኔ ሂደት፦ 1ኛ መሣሪያው በሌላ ሕገ ወጥ መንገድ ያልተገኘና የመንግሥት ንብረት ስለመሆኑ በፖሊስም በአቃቤ ሕግም መረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ፤ 2ተኛ ተከሳሹ መሣሪያውን የታጠቁት ያለ ፈቃድ መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል መሆኑን የሚደነግገው አዲሱ አዋጅ ከመውጣቱ ከብዙ ዓመታት በፊት እና የፓርላማ አባል በነበሩበት ወቅት መሆኑ ስለተረጋገጠ፣ ክሱ ውድቅ ተደርጎ ፍርድ ቤቱ በነፃ እንዳሰናበታቸው ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply