አቶ ልደቱ አያሌው ከእስር ተፈታ       አሻራ ሚዲያ   ታህሳስ 02/2013 ዓም ባህር ዳር የኢዴፓ ሊቀ መንበር አቶ አዳነ ታደሰ ለአሻራ ሚዲያ በስልክ እንደገለጹት ከሀጫ…

አቶ ልደቱ አያሌው ከእስር ተፈታ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 02/2013 ዓም ባህር ዳር የኢዴፓ ሊቀ መንበር አቶ አዳነ ታደሰ ለአሻራ ሚዲያ በስልክ እንደገለጹት ከሀጫ…

አቶ ልደቱ አያሌው ከእስር ተፈታ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 02/2013 ዓም ባህር ዳር የኢዴፓ ሊቀ መንበር አቶ አዳነ ታደሰ ለአሻራ ሚዲያ በስልክ እንደገለጹት ከሀጫሉ ግድያ ጋር በተያያዘ በደብረ ዘይት ዙሪያ ወረዳ ካፈው ሰኔ ወር መጨረሳ ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኘው አቶ ልደቱ አያሌው ዛሬ ታህሳስ 02 ቀን 2013 ዓ.ም ከእስር መፈታቱን ነግረውናል፡፡ አቶ ልደቱ አያሌው በእስር ላይ በነበሩባቸው ወራቶች በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት የቀረበ ቢሆንም በፍር ቤት ትዕዛዝ ከእስር ነጻ እንዲሆን ውሳኔ ያገኘ ቢሆንም በፖሊስ እምቢተኝነት እስካሁን ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በደብረ ዘይት ዙሪያ ወረዳ በእስር ለመቆየት መቻሉን ገልጸዋል፡፡ አቶ ልደቱ አያሌው በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት ሰእኔ የታሰርኩት ድንጋይ ወርዋሪ ኖሮኝ ሳይሆን በማራምደው ፖለቲካዊ ሀሳብ ብቻ ነው የሚል ምላሽ ሲሰጥ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ከሀያ ዓመታት በላይ ሰላማዊ ትግል በማድረግ የሚታወቅ የፖለቲካ ድርጅት ነው፡፡ ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply