አቶ ስብሃት ነጋ እና አቶ አባይ ወልዱን ጨምሮ በወንጀል የተጠረጠሩ 20 የህወሃት ቡድን አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥር 7 ቀን 2013 ዓ.ም…

አቶ ስብሃት ነጋ እና አቶ አባይ ወልዱን ጨምሮ በወንጀል የተጠረጠሩ 20 የህወሃት ቡድን አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 7 ቀን 2013 ዓ.ም…

አቶ ስብሃት ነጋ እና አቶ አባይ ወልዱን ጨምሮ በወንጀል የተጠረጠሩ 20 የህወሃት ቡድን አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አቶ ስብሃት ነጋ እና አቶ አባይ ወልዱን ጨምሮ በወንጀል የተጠረጠሩ 20 የህወሃት ቡድን አመራሮች ፍርድ ቤት ቀርበዋል። የፌዴራል መካከለኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በዛሬው እለት የቀረቡት የህወሃት ቁልፍ አመራሮች ከነበሩት መካከል አቶ ስብሃት ነጋ፣ አቶ አባይ ወልዱ፣ ዶክተር አብርሃም ተከስተ፣ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ ይገኙበታል። ተጠርጣሪዎቹ በሰሜን እዝ የአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ በደረሰው ጥቃት እንዲሁም ሌሎች ተደራራቢ የወንጀል ተግባራት የሚፈለጉ መሆኑን መርማሪ ፖሊስ ገልጿል። መርማሪ ፖሊስ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት 20 ተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ መጠየቁን ኢዜአ ዘግቧል። ፖሊስ በጠየቀው መሰረትም ፍርድ ቤቱ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል። ኢትዮ መረጃ ኒውስ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply