You are currently viewing አቶ ስንታየሁ ቸኮል እስካሁን ያሉበት አለመታወቁ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ…

አቶ ስንታየሁ ቸኮል እስካሁን ያሉበት አለመታወቁ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ…

አቶ ስንታየሁ ቸኮል እስካሁን ያሉበት አለመታወቁ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ እና የስራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኮል፤ የካቲት 1/2015 ዓ.ም ጠዋት ከጎፋ መካነ ህያዋን ቅዱስ ገብርኤል (ጎፋ ገብርኤል) ካቴድራል ለምህላ ከሄዱበት በፖሊስ እንደታገቱ ይታወሳል። ነገር ግን ወዴት እንደተወሰዱ ሊታወቅ አልተቻለም ሲል ባልደራስ አጋርቷል። በእለቱም ለብርበራ በፌደራል ፖሊስ ታጅበው ወደ ቤታቸው ተወስደው ነበር። ነገር ግን ፖሊሶቹ ወዴት እንደሚወስዷቸው ቢጠየቁም ለመናገር ፍቃደኛ አልሆኑም። ሜክሲኮ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ሊወሰዱ ይችላሉ የሚል ግምት የነበረ ቢሆንም፤ እዛ እንደሌሉ ለማወቅ ተችሏል። በተጨማሪም እስካሁን ፍ/ቤት ይቅረቡ/አይቅረቡ ማወቅ አልተቻለም። ባልደራስ እንዳጋራው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply