You are currently viewing አቶ ስንታየሁ ቸኮል የግል ፓስፖርታቸውን እንዳያሳድሱ የኤሚግሬሽን ዜግነት ጉዳይ አገልግሎት የከለከላቸው መሆኑ ተገለጸ።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ      ጥር 9 ቀን 2015 ዓ/ም…

አቶ ስንታየሁ ቸኮል የግል ፓስፖርታቸውን እንዳያሳድሱ የኤሚግሬሽን ዜግነት ጉዳይ አገልግሎት የከለከላቸው መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 9 ቀን 2015 ዓ/ም…

አቶ ስንታየሁ ቸኮል የግል ፓስፖርታቸውን እንዳያሳድሱ የኤሚግሬሽን ዜግነት ጉዳይ አገልግሎት የከለከላቸው መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 9 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ እና የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከባልደራስ ፓርቲ የትብብር ደብዳቤ ተጽፎላቸው የአስቸኳይ ፖስፖርት ማደሻ 2185 ብር የከፈሉ ቢሆንም ነገር ግን የእድሳቱን ሂደት ለመጨረስ ሲሞክሩ ተከልክለዋል። እንደ ምክንያት የቀረበባቸውም ነሃሴ 03/2014 ዓ.ም በአራዳ ምድብ ከፍተኛ ፍ/ቤት በዋለው ችሎት በ100 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ሲወሰን፤ በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ውጪ እንዳይወጡ ትዕዛዝ ተላልፎ ነበር። በዚህም መሰረት ከሀገር ውጪ በረራ እንዳያደርጉ ለኢሚግሬሽን ቢሮ ስማቸውና ፎቷቸው ተላልፏል። ይሁን እንጅ አራዳ ምድብ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ከሀገር እንዳይወጡ የበረራ ቪዛ እገዳ እንዲጣል እንጂ የፖስፖርት እድሳት እንዳያደርጉ አልከለከላቸውም። ነገር ግን በስርዓቱ ዘዋሪ ቁጥጥር ስር የዋለው የኢሚግሬሽን ዜግነት አገልግሎት ቢሮ አቶ ስንታየሁ ቸኮል የዜግነት መገለጫ የሆነውን ፓስፖርታቸውን ለማሳደስ በሄዱበት ሰዓት የእድሳት አስቸኳይ ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ እንደታገዱ አሳውቋቸዋል። ይህም መንግስት ሕግ በፈለገው መንገድ እየተረጎመ ለአፈና መጠቀሚያ ማድረጉን እንደቀጠለበት ግልፅ ማሳያ ነው ሲል ያጋራው ባልደራስ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply