You are currently viewing አቶ ስንታየሁ ቸኮል ጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችሎት ነፃ ቢላቸውም እስካሁን ከእስር አልተፈቱም። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ነሃሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ…

አቶ ስንታየሁ ቸኮል ጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችሎት ነፃ ቢላቸውም እስካሁን ከእስር አልተፈቱም። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ…

አቶ ስንታየሁ ቸኮል ጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችሎት ነፃ ቢላቸውም እስካሁን ከእስር አልተፈቱም። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ እና የፓርቲው ስራ አስፋፃሚ አባል የሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ነሃሴ 27/2014 ጠቅላይ ሰበር ይግባኝ ሰሚ ችሎት ቀርበዋል። መሰረታዊ የህግ ክፍተትን የሚመለከተው ጠቅላይ ሰበር ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ ዛሬም መርማሪ ፖሊስ በአቶ ስንታየሁ ቸኮል ላይ ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የስር ፍ/ቤቱን ውሳኔ አፅንቶታል። በውሳኔው መሰረት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ነሃሴ 27/2014 መፈታት ሲኖርባቸው እስካሁን ድረስ አለመለቀቃቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ወዴ ስንቄ ግልፀዋል። አቶ ስንታየሁ ቸኮል እስካሁን ድረስ ከ4 ወራት በላይ በዕስር የቆዩ ሲሆን ለዋስትና ብቻ ከ140 ሺህ ብር በላይ ከፍለዋል። አቶ ስንታየሁ ቸኮል የሶስት ሴት ልጆች አባት ሲሆኑ በቅርቡ በተረኛው ሥርዓት ለ 1 ዓመት ከ6 ወር ታስረው መለቀቃቸው ይታወሳል። አቶ ስንታየሁ እስካሁን ያልተፈቱት “ለሌላ ጉዳይ እንፈልጋቸዋለን”ተብሎ እንደሆነ ሰምተናል። የአዲስ አበባ ወጣት በፍፁም ጉዳዮን ሊያወግዝ ይገባል። በተመሳሳይ ነሃሴ 27/2014 ፍ/ቤት የቀረቡት ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጸሀፊ ታዲዎስ ታንቱ ለጥቅምት 14/2015 የተቀጠሩ ሲሆን የፍትህ መጽሄት ማኔጅንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ደግሞ ለጥቅምት 10/2015 ዓ.ም ተቀጥረዋል። ባልደራስ እንዳጋራው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply