You are currently viewing አቶ ስንታየሁ ቸኮል ፍ/ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም          አዲስ አበባ ሸዋ  የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የድርጅት ጉዳ…

አቶ ስንታየሁ ቸኮል ፍ/ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የድርጅት ጉዳ…

አቶ ስንታየሁ ቸኮል ፍ/ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ስንታየሁ ፖሊስ ማዘዣ አልደረሰኝም በማለት ሳያቀርባቸው ቀርቷል። ከዚህ ቀደም በነበረው ችሎት የተሰየሙት ዳኛ በዋስትና ጥያቄው ላይ መልስ ለመስጠት አልችልም በማለት ለአቃቤ ህግ ምላሽ እንዲሰጥ ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነበር። ሆኖም ግን ለአቃቤ ህግ ብቻ ሳይሆን ለፖሊስም የግፍ እስረኛውን ይዘው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ መሰጠት ነበረበት በሚል ፖሊስ ሳያቀርባቸው ቀርቷል። ጥቅምት 1/2015 ጠዋት በነበረው ችሎት ላይ ምናልባትም ፖሊስ ከሰዐት ሊያቀርባቸው ይችላል ተብሎ ለከሰአት ተቀጥሮ ነበር። ነገር ግን ከሰአትም ሳያቀርባቸው ቀርቷል። ስለዚህም ለጥቅምት 2/2015 የግፍ እስረኛውን ችሎት እንዲያቀርባቸው ለፖሊስ ትዕዛዝ ተፅፎ ተልኳል። በመሆኑም ነገ ጠዋት የመንግስ የግፍ እስረኛ የሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኮል በቡራዩ ከተማ ፍ/ቤት ይቀርባሉ። ባልደራስ እንዳጋራው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply