አቶ ተወልደ ገ/ ማርያም ለቦይንግ 737 ማክስ የቀረበውን ካሳ ወድቅ አንዲያረጉት ተጠየቁ

ከሁለት አመት በፊት ተከስክሶ 157 መንገደኞችን ለገደለው ለቦይንግ 737 ማክስ በቦይንግ ካምፓኒ የቀረበው 244 ሚልየን ዶላር ካሳ አጅግ ትንሽ የሆነ ሲሆን ይሄን የካሳ መጠን መቀበል በገንዘብም በፖለቲካም ክስረት ነው ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለዚሁ ጉዳይ የቀጠረው ችካጎ የሚገኘው ዲሲሎ ሊቪት ጉትዝለር የህግ አማካሪ ድርጅት የአየር መንገዱን ስራ አስኪያጅ አቶ ተወልደ ገ/ ማርያምን በደብዳቤ መጠየቁን ሲያትል ታይምስ ዘግቧል።
የህግ አማካሪው አቶ ተወልደን ድርጅታቸው በቦይንግ ላይ በአሜሪካ ክስ መስርቶ ብዙ ካሳ ሊጠይቅ ይገባል ለአውሮፕላኑ መከስከስ ቦይንግ ሙሉ ለሙሉ ተጠያቂ ነው ብሏል በደብዳቤው።
ለተጨማሪ ካሳ ዋናው ማስረጃም ፕሌኑ ለመከስከሱ ዋና ምክንያት የቦይንግ ቴክኒካል ሁለት ፓይለቶች ስለበረራ መቆጣጠርያው ሶፍትዌር በቂ መረጃ ለአየር መንገዱ በአለመስጠታቸው ነው ።ይሄን ጉዳይ ቦይንግም ያመነ ቢሆንም መጀመርያ ላይ ግን አንዳንድ የቦይንግ ከፍተኛ ሀላፊዎች ችግሩን በኢትዮጵያ አየርመንገድ ፕይለቶች ላይ ለማላከክ ሞክረው ነበር። ይሄም ወንጀል ነው። ከፍተኛም ካሳ ሊጠየቅበት ይገባል በማለት አቶ ተወልደን ክስ አንዲመሰረቱ ጠይቋል።
አማካሪው ድርጅት አንዳለው ገልልተኛ የሆነ ተቋም ባጠናው መሰረት አየር መንገዱ 1.8ቢልየን ዶላር ያለነሰ ገንዘብ በቦይንግ መከሰከስና እሱን ተከትሎ ባሳረፋቸው ቦይንግ ማክስ ፕሌኖችና ተያያዥ ጉዳዮች አጥቷል።

ሲያትል ታይምስ ለጉዳዩ ቅርበት አለው ብሎ በጠቀሰው ምንጭ ቦይንግ ከ500 አስከ 600 ሚልየን ዶላር ለአየር መንገዱ ለመክፈል ያቀደ ሲሆን ከዚህ ገንዘብ ላይ አብዛኛው ገንዘብ ግን ቦይንግ ፕሌኖችን በቅናሽና በረጅም ጊዜ ብድር ለአየር መንገዱ ለመሸጥ ያለመ ነው ።

The post አቶ ተወልደ ገ/ ማርያም ለቦይንግ 737 ማክስ የቀረበውን ካሳ ወድቅ አንዲያረጉት ተጠየቁ appeared first on Fidel Post.

Source: Link to the Post

Leave a Reply