አቶ ታዬ ደንደአ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እና የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት’ ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ በጸጥታ ሀይሎች ታህሳስ 2 ቀን በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደኣ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት” ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው።

በክሱ ላይ ፤ “ተከሳሹ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው ፀረሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በስማቸው በተከፈተ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ነበር” የሚል ተካቷል፡፡

አቶ ታዬ ደንደኣ በቁጥጥር ስር ሲውሉ በራሳቸው እና በቤተሰባቸው ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ገልጸው አቤቱታ በቃል አቅርበዋል። ምርመራው ታሕሳስ 24 ማለቁንና ዘግይቶ ክስ መቅረቡንም ተቃውመዋል።

ፍርድ ቤቱ ዋስትናውን በሚመለከት መርምሮ ብይን ለመስጠትም ለሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply