አቶ ታዲዮስ ጌታቸው በታጣቂዎች አልታገቱም!

የኩሪፍቱ ሪዞርት ባለቤት አቶ ታዲዮስ ጌታቸው በታጣቂዎች ታግተዋል በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ እየተዘዋወረ ይገኛል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኩሪፍቱ ሪዞርት ባለቤት የሆኑት አቶ ታዲዮስ ጌታቸው ላይ ደዉሎ እንዳረጋገጠዉ፣ ለስራ ጉዳይ በሱዳን እንደሚገኙና የሚባለዉ መረጃ ፍጹም ሃሰተኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

አቶ ታዲዎስ አክለዉም በቀጣይ በአርባ ምንጭ አካባቢ ለሚሰሩ ስራዎች ከአጋሮች ጋር ለመነጋገር ወደ ሱዳን ማቅናታቸዉን ተናግረዉ፣ እርሳቸዉን በሚመለከት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሚናፈሰዉን መረጃ እንደማንኛዉም ሰዉ ዛሬ ጠዋት አካባቢ መመልከታቸዉን ገልጸዋል፡፡

“እኔ ሰላም ነኝ”፤በሚወራዉ ነገር ለተደጋገጡና ትክክለኛዉ መረጃን ለማወቅ ለሚፈለጉ ሰዎች የምለዉም ይህንኑ ነዉ ብለዋል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ

መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply