አቶ ነብዩ ተድላ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙ

አቶ ነብዩ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ለ22 ዓመታት በዋናው መስሪያ ቤት እና ሚሲዮን ጽህፈት ቤቶች ሲሰሩ ቆይተዋል።

በተጨማሪም በምክትል ቃል አቀባይነት መስራታቸውም ተገልጿል።

አቶ ነብዩ በኒዮርክ፣ ሪያድ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሌሎችም ሀገራት እና ከተሞች በዲፕሎማትነት ማገልገላቸውን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።

አቶ ነብዩ በዛሬው ዕለት ከውጭ ጉዳይ ቋሚ ዘጋቢዎች ጋር ተዋውቀዋል።

መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply