
#አቶ አሸናፊ አካሉ ከስራ ተሰናበቱ ! የምዕራብ ጎጃም ዞን የአብን ከፍተኛ አመራር የሆኑት ታጋይ አሸናፊ አካሉ ከስራ ገበታቸው ተሰናበቱ! የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ በቅርቡ በአገዛዙ ስርዓት ከወህኒ ቤት በዋስትና የተለቀቁት አቶ አሸናፊ አካሉ በህግ ጥላ ስር በነበሩበት ወቅት መስሪያቤታቸው የስራ ስንብት ደብዳቤ አውጦባቸዋል። የአማራ ክልል መንግስት በክልሉ ግዥና ንብረት አስተዳደር ስልጠናና ሙያዊ ድጋፍ ባለሙያ የሆኑትን አቶ አሸናፊ አካሉ አበራን ከስራ ማሰናበቱን በደብዳቤ አሳውቋል። የክልሉ መንግስት ግዥና ንብረት ኦዲት ክትትልና ጥናት መረጃ ትንተና ዳይሬክቶሬት፡ አቶ አሸናፊ በስራ ገበታቸው አለመገኘታቸውን ገልፆ፡ ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ በተደጋጋሚ ጥሪ ባደርግም ምላሽ አልሰጡኝም ብሏል። በመሆኑም ከየካቲት 24/2015 ዓ/ም ጀምሮ ከስራ የተሰናበቱ መሆናቸውን የአማራ ድምፅ ዳይሬክቶሬቱ ከፃፈው ደብዳቤ ማረጋገጥ ችሏል። አቶ አሸናፊ ከወራት እስር ቦኋላ ሰሞኑን መፈታታቸው ይታወቃል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post