You are currently viewing አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በእስር ላይ የቆዩት አራቱ የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች ስለእስር ቤት ቆይታቸውን እና አፈታታቸው ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፤ ከጋዜጠኞች ለተነሱ በ…

አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በእስር ላይ የቆዩት አራቱ የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች ስለእስር ቤት ቆይታቸውን እና አፈታታቸው ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፤ ከጋዜጠኞች ለተነሱ በ…

አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በእስር ላይ የቆዩት አራቱ የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች ስለእስር ቤት ቆይታቸውን እና አፈታታቸው ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፤ ከጋዜጠኞች ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ምላሽም ሰጥተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 5 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከፍተኛ አመራሮች እነ አቶ እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ቀለብ ስዩም እና አስካለ ደምሌ አንድ ዓመት ከመንፈቅ ገደማ ስለነበራቸው የእስር ቤት ቆይታ እና ስለአፈታታቸው እንዲሁም በወቅታዊ ጉዳይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። ጋዜጣዊ መግለጫው የተሰጠው በርካታ የመገናኛ ብዙሃን በተገኙበት ስድስት ኪሎ በሚገኘው በባልደራስ ዋና ጽ/ቤት ነው። ጥር 5 ቀን 2ዐ14 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ በተሰጠው መግለጫ ክስ ተቋርጦ የተፈቱት እነ እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ቀለብ ስዩም እና አስካለ ደምሌ ተገኝተው ስለቆይታቸውና ስለአፈታታቸው ማብራሪያ ሰጥተዋል። ጋዜጣዊ መግለጫው ከተነበበ በኋላ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ስንታየሁ ቸኮል፣ ቀለብ ስዩም እና አስካለ ደምሌ ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። የፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋም ሆኑ በመድረኩ ተገኝተው ማብራሪያ የሰጡ አመራሮች ሀገርን የማዳን እና የኢትዮጵያ አንድነትን የማስጠበቅ ጉዳይ ከሁሉም በፊት ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፤ ይህም የፓርቲያቸው ባልደራስ አላማ መሆኑን ገልጸዋል። አሚማ በስፍራው ተገኝቶ ዝግጅቱን ተከታትሏል፤ በዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ። 15:49 Reply Copy Selected Text Pin Forward Select Report Delete A Abay የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በቅርቡ ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ለተፈቱት ለግፍ እስረኞች ለእነ እስክንድር ነጋ እና ባጋጠማቸው ህመም በውጭ ሀገር በህክምና ክትትል ቆይተውና አገግመው ለተመለሱት ለአቶ ማሙሸት አማረ ደማቅ አቀባበል አደረገ፤ ለከፈሉት ዋጋም ከፍ ያለ ምስጋና አቅርቧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 5 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በቅርቡ ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ለተፈቱት ለግፍ እስረኞች ለእነ እስክንድር ነጋ እና ባጋጠማቸው ህመም በውጭ ሀገር በህክምና ክትትል ቆይተው እና አገግመው ለተመለሱት ለአቶ ማሙሸት አማረ አቀባበል አድርጓል። ዝግጅቱን በዋናነት ተጋባዥ እንግዶች፣ የፓርቲው አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች በተገኙበት በድምቀት እንዲከናወን ያደረጉት የመኢአድ አዲስ አበባ ስራ አስፈጻሚዎች ናቸው። በእለቱም በትግሉ ለተሰው ጓዶችና በተለያዩ አካባቢዎች እየተገደሉ ላሉ ንጹሃን የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ከተደረገ በኋላ የመኢአድ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት በፓርቲው ስም ለሁለቱም የፓርቲ ፕሬዝዳንቶች እና ከእስር ለተፈቱት ለሌሎች ለባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ቴዎድሮስ አደባባይ በሚገኘው በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ዋና ጽ/ቤት ጥር 5 ቀን 2014 ተገኝቶ የተደረገውን የክብር አቀባበል ተመልክቷል። ለ1 ዓመት ከ6 ወር በአስከፊው እስር ከቆዩ በኋላ ታህሳስ 29 ቀን 2014 ክሳቸው መቋረጡን ተከትሎ የተፈቱት የባልደራስ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ፣ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ቀለብ ስዩም እና አስካለ ደምሌ እንኳን ተፈታችሁ በሚል የክብር አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በእስር ቤት ሆነው ለከፈሉት መስዋዕትነትና ላሳዩት ጽናት ከመድረክ ከፍ ያለ ምስጋና ቀርቦላቸዋል፤ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ ያለው የአንገት እስካርፕም በመኢአድ ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት በአቶ አብርሃም ጌጡ በኩል ተሸልመዋል። በተጨማሪም ባጋጠማቸው ህመም ወደ ውጭ ሀገር ሄደው የህክምና ክትትል በማድረግ አገግመው በሰላም ለተመለሱት ለመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረም እንኳን ደህና መጡ ተብለዋል፤ እስካሁን በጽናት ለድርጅቱና ለሀገር ላበረከቱት በጎ አስተዋጽኦም ተመስግነዋል፤ ተሸልመዋልም። በመድረኩም የሁለቱም ፓርቲ ፕሬዝዳንቶች አቶ እስክንድር ነጋ እና አቶ ማሙሸት አማረ እና የመኢአድ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበ ንግግር አድርገዋል። አቶ እስክንድር ነጋ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ካለፉት በርካታ ዓመታት ጀምሮ በነበረው ትግል ከመሰረቱ ሳይለቅ በጠንካራ አለት ላይ ተመስርቶ በትግሉ እየቀጠለ ያለ ድርጅት መሆኑን ጠቅሰው ምስጋና አቅርበዋል። ለዚህ ሁሉ የአንድነት ትግል መሰረቱ ግን እነ ፕሮፌሰር አስራት ወልደዬስ እና ኢ/ር ኃይሉ ሻወል መሆናቸውን አስረግጠው ተናግረዋል። በተመሳሳይ የመኢአድ ፕሬዝደንት አቶ ማሙሸት አማረም ከባልደራስ ፕሬዝዳንት ከእነ እስክንድር ነጋ ጋር በመሆን ሁለቱ ፓርቲዎች ወደ አንድ በመምጣት ትግሉን ወደላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግሩ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፤ ለጀግኖቹም እንኳን ተፈታችሁ ብለዋል። በዝግጅቱም የዳቦ ቆረሳ ስነ ስርዓት እና የምሳ ግብዣ መደረጉን ተመልክተናል። ሙሉ ዝግጅቱን በአሚማ የዩቱብ አድራሻ የምናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply