አቶ እስክንድር ነጋ በቀረበው ክስ ላይ ምስክሮች ከበስተጀርባ እና ማንነታቸው ሳይታወቅ ይመስክሩ የሚለውን አካሄድ ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ ያፈነገጠ እና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ በቃል መቃወ…

አቶ እስክንድር ነጋ በቀረበው ክስ ላይ ምስክሮች ከበስተጀርባ እና ማንነታቸው ሳይታወቅ ይመስክሩ የሚለውን አካሄድ ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ ያፈነገጠ እና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ በቃል መቃወ…

አቶ እስክንድር ነጋ በቀረበው ክስ ላይ ምስክሮች ከበስተጀርባ እና ማንነታቸው ሳይታወቅ ይመስክሩ የሚለውን አካሄድ ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ ያፈነገጠ እና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ በቃል መቃወሚያ ሰጡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አቶ እስክንድር ነጋ በቀረበው ክስ ላይ ምስክሮች ከበስተጀርባ እና ማንነታቸው ሳይታወቅ ይመስክሩ የሚለውን አካሄድ ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ ያፈነገጠ እና ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ ነው በቃል መቃወሚያ የሰጡበት። አማራ ሚዲያ ማዕከል ያነጋገራቸው የእነ አቶ እስክንድር ነጋ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ እንደገለፁት ትናንት ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም በቅርብ ጊዜ የተመሰረተባቸው ክስ የምስክር አሰማም ሂደት ምን መምሰል እንዳለበት ክርክር ተካሂዶበታል። አቶ እስክንድር ነጋ በተለይ ደግሞ ህዝብን ከህዝብ፣ ሀይማኖትን ከሀይማኖት በማጋጨት ተብሎ በሚመሰረት ክስ ላይ የሚቀርብ የምስክር ሂደት ግልፅ፣በሰዎች ዘንድ አስተማሪና ተመዛኝ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል። ከበስተ ጀርባ፣ማንነታቸው ሳይታወቅና ዝርዝራቸውም ለተከሳሾች ሳይገለፅ የሚከናወን የምስክር ሂደት የፍትህ ሂደቱን አጠቃላይ ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ እንደሚሆን አስረድተዋል። አቶ እስክንድር ነጋ ባቀረቡት ሰፋ ያለና ተዘጋጅተው በቀረቡበት የመቃወሚያ ሀተታ ህዝብን ከህዝብ፣ብሄርን ከብሄርና ሀይማኖትን ከሀይማኖት በማጋጨት በሚል የሚመሰረቱ ክሶችን ዓለም አቀፍ ተሞክሮን በዳሰሳ መልክ ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አብራርተዋል ነው የተባለው። እንደአብነትም በሩዋንዳ፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይም በአይሁዶች ላይ የተመፈፀመውን የዘር ማጥፋትን በተመለከተ እንዲሁም በሀገራችን በደርግ ዘመን በቀይ ሽብር ወንጀል ተመስርተው የነበሩ የዘር ማጥፋት ክሶችን በማስታወስ ሁሉም የምስክር ሂደቶች በግልፅ ችሎት የተሰሙ መሆናቸውን ገልፀዋል። በመሆኑም ችሎቱ በምንም ዓይነት መንገድ ፍትህ እንዲደበቅ ማድረግ እንደሌለበት አቶ እስክንድር አፅንኦት ሰጥተው አሳስበዋል። ሌላኛዋ የባልደራስ አመራር ወ/ሮ ቀለብ/አስቴር ስዩም በዋናነት አቃቢ ህግ ማንነታቸውን ሳልገልፅ ከመጋረጃ በስተጀርባ ይመስክሩልኝ እንዳለው እኛ ተከሳሾችስ በተመሳሳይ በአቃቢ ህግ ላይ ምስክሮችን ስናቀርብበት ማንነታቸውን ሳናሳውቅ ከመጋረጃ በስተጀርባ ደብቀን ይሰማ ብንል ይፈቀድልናል ወይ ሲሉ ችሎቱን ጠይቀዋል። በመጨረሻም እስከ አንድ ወር ከ20 ቀን የሚቆይ ረዥም ቀጠሮ ማለትም ለህዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም መባሉ የባልደራስ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች አባሪዎቻቸው ከፍተኛ ቅሬታ ያነሱበት ጉዳይ ነበር። ጉዳዩ የተፋጠነ ፍትህ ካላገኘ በተለይ በዚህ ዓመት በሚደረገው ምርጫ ለመሳተፍ ያላቸውን እድል በእጅጉ የሚያጣብብ መሆኑንም ተከሳሾቹ ስለማንሳታቸው ነው ጠበቃ ሄኖክ የተናገሩት። የፍርድ ቤቱ አስተዳደር ችግሩን እንዲፈታ የጠየቀ መሆኑን የገለፀው ችሎቱም ለተነሳው ቅሬታ በጣም ብዙ መዝገቦች ስላሉብን ማድረግ የምንችለው ነገር ይሄን ነው በማለት የቀጠሮ ማስተካከያ አላደረገም፤ የተፋጠነ ፍትህ ለመስጠት ከአቅሙ በላይ እንደሚሰራ ግን አስታውቋል። የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎትም በቀጣይ ቀጠሮው በምስክር ሂደቱ ምን መምሰል አለበት በሚለው ላይ በአቃቢ ህግ እና በተከሳሾች እንዲሁም በጠበቃ በኩል በቃልና በፁሁፍ የቀረቡ የመከራከሪያ ሀሳቦችን መዝኖ ብይን የሚሰጥበት ይሆናል ተብሏል። መዝገቡ የሚጠራው በአቶ እስክንድር ነጋ ሲሆን 7 ተከሳሾችን ያካተተ ነው፤ አራቱ የባልደራስ ሰዎች፣አንድ ከባልደራስ ውጭና ሁለቱ ደግሞ በሌሉበት የተከሰሱ መሆናቸው ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply