አቶ እስክንድር እና አቶ ስንታየሁ ወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተዘዋወሩ!

የባልደራስ ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋ እንዲሁም የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከዚህ ቀደም ታስረውበት ወደ ነበረው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት መዛወራቸውን ጠበቃቸው ሔኖክ አክሊሉ ለቢቢሲ (BBC) ገልፀዋል።

ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ ለBBC ከተናገሩት ፦

– ሁለቱ ተጠርጣሪዎች (አቶ እስክንድርና አቶ ስንታየሁ) ብቻ ሳይሆኑ ሌላ አንድ ግለሰብም ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተወስደዋል።

– ጳጉሜ 5/2012 ዓ.ም በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ላይ አቶ እስክንድር ላይ ክስ ተመስርቶ ነበር ፤ ፍርድ ቤት ክስ የቀረበባቸው በመሆኑ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ አዟል።

– በትናንትናው ዕለት መስከረም 06/2013 ዓ/ም ከነበሩበት የፌደራል ፖሊስ ጊዜያዊ ማቆያ ወደ አዲስ አበባ ማረሚያ ቤት በተለምዶ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ወደ ሚባለው ተዘዋውረዋል።

– አቶ እስክንድር ከዚህ ቀደም ከስድስት ዓመታት በላይ በታሰሩበት ስፍራ እና ክፍል ዳግም መታሰራቸውን ተናግረዋል።

– አቶ አስክንድር ከሁለት ወራት በላይ ከቆዩበት ሌላ እስር ቤት ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከተዘዋወሩ በኋላ በተለምዶ ዋይት ሐውስ ወደ ሚባለው ክፍል አስገብተዋቸዋል።

@tadiyasaddis

Leave a Reply