You are currently viewing አቶ ክርስቲያን ታደለ “…ድክመትን ውጫዊ ማድረግና በግልጽ የአማራ ብሔር ማኅበራዊ እሴቱ የሆነውን ፋኖነነት ያልተገባ ጭቃ መቀባቱ አማራ ጠልነት ነው።” ሲል በወ/ሮ አዳነች አበቤ ሰሞነኛ…

አቶ ክርስቲያን ታደለ “…ድክመትን ውጫዊ ማድረግና በግልጽ የአማራ ብሔር ማኅበራዊ እሴቱ የሆነውን ፋኖነነት ያልተገባ ጭቃ መቀባቱ አማራ ጠልነት ነው።” ሲል በወ/ሮ አዳነች አበቤ ሰሞነኛ…

አቶ ክርስቲያን ታደለ “…ድክመትን ውጫዊ ማድረግና በግልጽ የአማራ ብሔር ማኅበራዊ እሴቱ የሆነውን ፋኖነነት ያልተገባ ጭቃ መቀባቱ አማራ ጠልነት ነው።” ሲል በወ/ሮ አዳነች አበቤ ሰሞነኛ ንግግር ላይ ትችት አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 2 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የሕዝብ እንደራሴ አቶ ክርስቲያን ታደለ ፀጋዬ ከንቲባ አዳነች አበቤ በአዲስ አበባ የተለያዩ ት/ቤቶች ከሰሞኑ በኃይል የኦሮሚያ ክልል ባንዴራን ከመስቀል እና የክልሉን መዝሙር ከማዘመር ጋር በተያያዘ እያጋጠመ ያለውን ግጭትና ተቃውሞ በተመለከተ ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውንና በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ማጋራታቸውን ተከትሎ የሰጠው አስተያየት የሚከተለው ነው:_ ሰላም ክብርት ከንቲባ፣ በመጀመሪያ ከተማሪ ወላጆችና ጉዳዩ ካሳሰባቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ከሰሞኑ በከተማችን በተፈጠረው የትምህርት ማኅበረሰብ ችግር ዙሪያ ውይይት ማድረጋችሁን በበጎ የምመለከተው ነው። በመቀጠል ያሉኝን ጥያቄዎች አቀርባለሁ። አዲስ አበባ የፌዴራሉ መንግስት ዋና ከተማና በሕገመንግስቱ አንቀጽ 49 መሰረት ራሷን ሙሉ በሙሉ የማስተዳደር ነፃነት ያላት ከተማ ነች። ይኼ እውነት በሥራ ላይ ባለው ሕገመንግስት የተቀመጠ ነው። የከተማ አስተዳደሩ የተሻሻለው ቻርተርም ይህንኑ እውነት የሚያስረግጥ ነው። የኦሮሚኛ ቋንቋ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ፍላጎቱ ላላቸው ተማሪዎች መሰጠቱም መጥፎ አይደለም። (እንኳንስና የአገራችንን የራሳችንን የኦሮሚኛ ቋንቋ ቀርቶ ባሕር ተሻግረን እንግሊዝኛን ጨምሮ ልዩ ልዩ ቋንቋዎችን እየተማርን አይደለም ወይ! ) ይሁንና የከተማ አስተዳደሩ በካቢኔም ሆነ በክልሉ ምክርቤት ሳያስወስን፤ የተማሪዎችና ወላጆቻቸው ይሁንታ ሳይታከልበት ተማሪዎችን በግድ አንድን ቋንቋ ተማሩ ማለት ተገቢም፥ ትክክልም አይሆንም። ከዚህ የከፋው ደግሞ የአዲስ አበባ ተማሪዎችን ያለፍላጎታቸውና ከሕግ ውጭ የአንድን ክልል መዝሙር እንዲዘምሩና ሰንደቅ እንዲያውለበልቡ መገደዳቸው ነው። በየትኛው አሰራር ነው ካሪኩለም የሕገመንግስትን ድንጋጌ የሚሽረው? አዲስ አበባ የፌዴራሉ መንግስት ዋና ከተማ ነው ማለት የሁሉም የፌዴሬሽኑ አባላት ከተማ ነው ማለት ነው። የሁሉም በሆነ ጉዳይ ላይ የአንዱን ፍላጎት ብቻ ነጥሎ ማክበር በምን መልኩ ልክ ሊሆን ይችላል? የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ራሱን የቻለ መንግስት አይደለም ወይ? ሁሉም ክልሎች ተመሳሳይ ሰንደቅ ይውለብለብልን፥ መዝሙር ይዘመርልን ጥያቄ ቢያነሱ ተማሪዎች የአስራ ምናምን ክልሎችን ሰንደቅ ሲሰቅሉና መዝሙር ሲዘምሩ ትምህርት በምን ትርፍ ጊዜያቸው ሊማሩ ነው? የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰንደቁን ማውለብለብና መዝሙሩን ማስዘመር ከፈለገ ለምን በራሱ ወጪ መሰል ትምህርት ቤቶችን ገንብቶ በራሱ አያስተዳድርም? ከላይ ያነሳኋቸው መሰረታዊ ግን አስተውሎትን የሚጠይቁ ጥያቄዎችን አመራሩ መመለስ ይኖርበታል። መሰል የአግባብነት ጥያቄዎችን በመመለስ ፋንታ ድክመትን ውጫዊ ማድረግና በግልጽ የአማራ ብሔር ማኅበራዊ እሴቱ የሆነውን ፋኖነነት ያልተገባ ጭቃ መቀባቱ አማራ ጠልነት ነው። ይህ ደግሞ መንግስታዊ ኃላፊነትን ከወሰደ አንድ አመራር የሚጠበቅ ካለመሆኑም ባሻገር ነውርም፥ ወንጀልም ነው። በአመራር ልግመትና ስንፍና የሚጠሩ የሕዝብ ጥያቄዎችን በሙሉ የምዕራባውያን እጅ ያለበት አስመስሎ ማቅረብም ትክክል አይደለም። መሰል ያልተገሩ የአመራር ንግግሮች በዲፕሎማሲው ረገድ አገራችንን ብርቱ ዋጋ አስከፍለዋል። እናም ከዚህ አንፃር ደግመን ደጋግመን ከስሜት በፀዳ መልኩ የኮሚዩኒኬሽም ሥራዎችን ልናደርግ ይገባል። በተረፈው ሰላም የሁሉም ዜጎች መሻት ነውና፤ ሁላችንም ለጋራ ሰላማችን እንትጋ። በተለይ በአመራር ደረጃ ያላችሁ ሁሉ ግጭትን ከመጥመቅ ትቆጠቡ ዘንድ መልእክቴን አስተላልፋለሁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply