አቶ ደመቀ መኮንን ከመንግስት እና ከገዢው ፓርቲ ከነበራቸው ኃላፊነት ተሰናበቱ

ላለፉት 11 ዓመታት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት ደመቀ መኮንን፤ ከመንግስት እና በገዢው ፓርቲ ከነበራቸው ኃላፊነት መሰናበታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለcኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። አቶ ደመቀ በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትነት በነበራቸው የኃላፊነት ቦታ ላይ፤ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ መተካታቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።

ላለፉት አራት ዓመታት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ስራን ደርበው ሲሰሩ የቆዩት አቶ ደመቀ፤ ከትላንት በስቲያ ጀምሮ ሲካሄድ በነበረው የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ “በክብር መሸኘታቸውን” ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል። አቶ ደመቀ ከኃላፊነታቸው ተሰናብተው ወደ ተሰብሳቢዎች መቀመጫ ሲያመሩ፤ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ከመቀመጫቸው በመነሳት በጭብጨባ ሲቀበሏቸው በፎቶግራፎች ታይቷል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

[በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች ይታከሉበታል]

Source: Link to the Post

Leave a Reply