አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተላከ መልዕክት ለሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር አደረሱ

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተላከ መልዕክት ለሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር አደረሱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፊዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳጋቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር አደረሱ።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔት በተመለከተ የተላከ መልዕክት ለሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሌትናልት ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና ለሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ አድርሰዋል::

በዚሁ ወቅት ባደረጉት ውይይት ለሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሌትናልት ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና ለሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት ያላቸውን ሙሉ ድጋፍ አረጋግጠዋል።

ችግሩ ባጠረ ጊዜ እልባት ሊያገኝ እንደሚችል እምነታቸው መሆኑንም መግለፃቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

The post አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተላከ መልዕክት ለሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር አደረሱ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply